ጥቅምት 24/2014 ዓም በሀገራችን መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ በሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ከጀርባው የተወጋበትን 1ኛ ዓመት በማስመልከት ለተሰው ጀግኖች የ1 ደቂቃ የህሊና ጸሎት ስነ ስርዓት በጉራጌ በተለያዩ አካባቢዎች ተካሔደ።

ተሳተፊዎቹም ጀግኖች የከፈሉት መሰዋአትነት እስከመቼም አንረሳውም!፣ሁሌም ከመከላከያው ጎን ነን!፣ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆችዋ ተከብራ ትኖራለች ሲሉም ገልፀዋል።

በዞኑ የሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ሴክተር መስሪያቤቶች በእዙ ላይ የደረሰውን ጥቃት በማውገዝ እለቱን አስበውታል፡፡

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ እለቱን ሲያስቡት እንደገለጹት የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየከፈለ ያለውን መሰዋትንት በማሰብ ሁሉም ዜጋ ሀገራችን ላይ እየተካሄደ ያለውን ሴራ ማውገዝ እንዳለበት እና ይህንን ፈተና ሁሉም ህብረተሰብ ተባብሮ ማለፍ እንዳለበት ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በጥቅምት 24/2023 ዓ.ም መሰዋት የሆኑ የሰራዊት አካላት በማሰብ የቡድኑን ክህደት በማስታወስ በእለቱ ከ3፡00 ሠዓት ጀምሮ ቀኝ እጃችንን ደረታችን ላይ ለ45 ሰከንድ በማድረግ እለቱ ታሳቢ ሆኖ እንዲውል ተደርጓል ብለዋል።

አቶ አሰፋ አካሉ አክለውም ችግሩ ከተፈጠረ ጊዞ ጀምሮ የዞኑ ማህበረሰብ በገንዘብ፣ስንቅ በማዘጋጀትና የእርድ ሰጋዎች በመስጠት እንዲሁም አስከ ግንባር በመዝመት የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱን ተናግረዋል።

አቶ ጀማል አህመድ እንደገለፁት የህውሀት የጥፋት ቡድን በመከላከያና በንፁሀን ህዝብ ላይ ያደረሰው ጥቃት ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባር በመሆኑ ሊወገዝ ይገባል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የህዝቦችን ደህንነት ለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃ ተገቢ በመሆኑ መላው ህብረተሰቡ ከፀጥታው አካል ጎን ተሰልፎ ማገዝ አለበት ብለዋል፡፡

አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ሰርጎ ገቦችን ለፀጥታ አካት አሳልፎ መስጠት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

አቶ አብራር መውደድ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ሰራተኛ ሲሆኑ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የደረሰው ጥቃት ታስቦ መዋሉ ተገቢ እንደሆነና በቀጣይም መላው የሀገሪቱ ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጐን መሰለፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመታሰቢያ መረሃ ግብሩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ወጣቶችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *