ግብርና ታክስ በወቅቱ በመሰብሰብ ህብረተሰቡን የሚጠይቃቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚሰራ የእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ነሐሴ 20/2014

ግብርና ታክስ በወቅቱ በመሰብሰብ ህብረተሰቡን የሚጠይቃቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚሰራ የእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ በ2014 የግብር ዘመን ከ86ሚሊዮን 4መቶ 2ሺ ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ጠቁሟል።

የእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኩመል ኤሊያስ በወረዳው በ2014 በጀት አመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 80ሚሊዮን 5መቶ 85ሺ 4መቶ 99 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 86ሚሊዮን 4መቶ 2ሺ 2መቶ 49 ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል። በዚህም የእቅዱ 107 ከመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

በወረዳው ከ3ቱም ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 1ሚሊዮን 5 መቶ61ሺ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 2ሚሊዮን 1መቶ 42 ሺ 462 ብር መሰብሰብ ተችሏል።

ይህም ከተመሳሳይ አመት ጋር ሲነፃፀር 22ሚሊዮን 2መቶ22ሺ 1መቶ 25 ብር ብልጫ እንዳለውም አመላክተዋል።

የገቢው ማደግ ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በተለያዩ አማራጮች ግብዛቤ በመፈጠሩ፣ የተቋሙ ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነትና ስነ ምግባር፣ የማኔጅመንት አካላት ተሳትፎና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር የተጠናከረ በመሆኑ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር አድርጎታል ብለዋል።

በ2014/15 የግብር ዘመን በወረዳው 5መቶ81 የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ አሳውቀው መክፈላቸውን ገልጸው በዚህም 4ሚሊዮን 196ሺ 485 ብር በመሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

እንደ ኃላፊ ገለጻ በወረዳው 9 የደረጃ ለና 6 የደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች እንዳሉ ገልጸው ያለምንም ቅጣት በወቅቱ ታክሳቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በወረዳው ከገቢ ስወራ አንፃር የግብርና ምርቶች በህገወጥ የንግድ ስርአት እንዳይወጡና ህጋዊ ስርአት ተክትለው እንዲወጡ በ4ቱም ማዕከላት የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በ2014 በጀት አመት ያለ ደረሰኝ ግብይት ሲፈፅሙ የተገኙ ግለሰቦች ላይ 2 የጽሁፍ ማስጠንቀቁያ መሰጠቱ ጠቁመው በተመሳሳይ 1የደረጃ ሐ ግብር ከፋይ 50ሺ ብር እንዲቀጣ መደረጉንም ተናግረዋል።

በደረሰኝ ከመገበያየት ጋር ተያይዞ ውስንነት መኖሩ የተናገሩት ኃላፊው በደረሰኝ ምንነትና ጠያቂ ማህበረሰብ ለመፍጠር በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ግብርና ታክስ በወቅቱ በመሰብሰብ ህብረተሰቡን የሚጠይቃቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግብርን ያለ ቅጣትና እንግልት በወቅቱ መክፈል እንዳለባቸው ያነሱት አቶ ኩመል ለዚህም ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *