ጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

ጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰብሳቢ ኡስታዝ አባስ ያሲን በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ፈጣሪ ከሚደሰትባቸው ነገሮች ትልቁና በላጩ ሰዎች ከወንጀልና ከክፋት ነፃ ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው መቅረብ በመቻላቸው ነው ብለዋል።

ኢድ አልፈጥር ህዝበ ሙስሊሙ 30 ቀናት ፆሞ ተክባህ ወደ ሚባል ከፍተኛ የስብዕናና የስነ ምግባር ደረጃ ላይ በመድረስ፣ ለፈጣሪው በጣም ቅርብ ሆኖ ፆሞ፣ ኢባዳውን አጠናቆ የሚደሰትበት ቀን መሆኑን አስረድተዋል።

በኢድ በዓል ከሚወደዱ ተግባራት አንዱ ተክቢራ መሆኑን የገለጹት ኡስታዝ አባስ አላህን ከፍ አድርጎ በማውሳት፣ ቤተሰብ ወዳጅና ዘመድ አዝማድ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት በመግለጽ በደስታ ይከበራል ብለዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥር በዓል ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ ከቤተሰብ ጋር አብሮ በማሳለፍ እና በማህበረሰቡ ልብ ውስጥ ደስታ እንዲፈጠር ማድረግ ይጠበቅበታል።

በረመዳን ወር ከምግብና ከመጠጥ በመቆጠብ ወደ ፈጣሪው ለመቅረብ የሚተጋበት ወቅት ከመሆኑ በተጨማሪ የሰው ልጅ በስነ ምግባር እንዲታነጽ፣ ራሱን እንዲገዛ፣ ሌሎች ወገኖቹን እንዲረዳ የሚያስችል በመሆኑ አመቱን ሙሉ ረመዳን በማድረግ በጎ ተግባራት መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የተቸገሩትን መርዳት፣ ሰላማዊ መሆን፣ መልካም ስነ ምግባር መላበስ የአንድ ወቅት ተግባር ባለመሆናቸው እስከ ህይወት ፍጻሜ ድረስ መተግበር ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመጨረሻም ኡስታዝ አባስ ያሲን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1445ኛዉ የኢድ አል ፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሠላም፣ የፍቅርና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

      መልካም የኢድ አል ፈጥር በዓል!!!
               ኢድ ሙባረክ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *