ገጨቅዱስሩፋኤልአንድነትገዳም

ነሐሴ29/2014 ዓ.ም

ገጨቅዱስሩፋኤልአንድነትገዳም

ጉራጌ ዞን በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ሰው ሰራሽና ታሪካዊ ቅርሶች ከብሄረሰቡ ባህላዊ እሴቶች ጋር ተዳምረው ልዩ ገጽታ እንዲላበስ አድርገውታል፡፡ በዞኑ ከሚገኙ ጥንታዊና ኃይማኖታዊ ቅርሶች መካከል የገጨ ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም አንዱ ነው፡፡

ገዳሙ በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በዴሰነ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ወልቂጤ 42 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከወረዳው ርዕሰ ከተማ አገና ሳይደርስ 1ነጥብ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከዋና መንገድ ዳር ደሳለኝ ሎጅ ፊትለፊት ይገኛል፡፡

ገዳሙ የሚገኝበት አካባቢ ማራኪ፣ በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ከገዳሙ ፊት ለፊት የሚገኘው ዘመናዊውና ደረጃውን የጠበቀ ደሳለኝ ሎጅ ሥፍራው ልዩ የቱሪስቶች መዳረሻ ያደርገዋል፡፡.

የገጨ ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም ጥንታዊ ይዘት ቢኖረውም ሥራ ላይ የዋለው ግን የቆጠር ገድራ ገዳም በራዕይ የተገለፀላቸው ባህታዊው አባ ገብረክርስቶስ ባዩት ራዕይ መሰረት ታህሳስ ወር 2005 ላይ ሲሆን ባህታዊው በዚህ ቦታ ታሪካዊ ቅርሶች በስፍራው እንደሚገኝ ለሚመለከታቸው የቤተክህነትና የመንግስት ኃላፊዎች ከገለፁ በኋላ ከአጎራባች ወረዳዎችና ከአከባቢው የተሰበሰበ ህዝብ፤ የመንግስት ኃላፊዎች፤ የኃይማኖት አባቶችና የሚዲያ አካላት በተገኙበት ጫካው ተመንጥሮ በቁፋሮ ቅርሶቹ እንደተገኙ የገዳሙ አስተዳዳሪ ይገልፃሉ፡፡

በቁፋሮ የተገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገልገያ የሆኑ ቅርሶች የብረት ደወል፣ የብራና ስዕላት፣ ማዕጠንት/ጥና/፣ በድንጋይ ላይ የተቀረፁ መስቀሎች፣ ከቆይታ ብዛት በአፈር የተባለ የእንጨት መስቀል/እርፋ መስቀል/፣ በእምነበርድ ድንጋይ ላይ በፍሬም የተቀረፁ ምስሎችና ፅላቶች በገዳሙ ይገኛሉ፡፡..

በአሁኑ ወቅት በእዣ ወረዳ አስተዳደር እና በአካባቢው ህብረተሰብ አማካኝነት ቅርሶቹ በተገኙበት ሥፍራ በጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ውስጥ ጥበቃ እየተደረገላቸውና በቱሪስቶችም እየተጎበኙ ይገኛሉ፡፡
ገዳሙ አዲስ እንደመሆኑ መጠን በደንብ መልማት የሚገባው ሲሆን በስፍራው የተገኙት ታሪካዊ ቅርሶችን የቱሪስት መስህብ ከመሆናቸው ባለፈ ለአካባብው የገቢ ምንጭ ከመፍጠር አንፃር የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ለገዳሙ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *