የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት የ2014 በጀት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ጉባኤ እና ስልጠና መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል ።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምርያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት በዞኑ የሚገኙ የህብረት ስራ ዩኒየኖች እና ማህበራት ግብርናውን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና ስላላቸው ማጠናከርና መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመሆኑም አርሶ አደሩ ከምርት ብክነት ለመታደግ 48 ኮምባይነሮች በዩኒየኖች በኩል ማስገባቱ ያስታወሱት አቶ አበራ ይህ ቢሆንም ያለውን ምርት በፍትዊነት ለማስኬድና ገበያውን ለማረጋጋት ህገ ወጥ ነጋዴዎችና ደላሎች ላይ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ነው ያሉት።
ገበያውን ለማረጋጋትና የማህበረሰቡ ችግር ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአርሶ አደሩ ዘንድ ለቅሬታ የሚቀርበው የማዳበሪያ ስርጭትና ብድር አመላለስ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ማረምና አሰራሩ ማዘመን እንዳለበት መክረዋል።
የጉራጌ ዞን ህብረት ስራ ልማት ጸ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ በበኩላቸው የህብረት ስራ ማህበራት የግብርና ግብአት ለህብረተሰቡ በማቅረብ፣ ምርታማነት እንዲሻሻልና በተመረተው ምርት ፍትሀዊ ግብይት እንዲኖር፣የስራ እድል በመፍጠር፣ ለኢንቨስትመንት የቁጠባ እና የብድር አቅርቦት የማመቻቸት ስራዎች እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል ።
ማህበራቶቹ ወቅቱን የሚመጥን ስራዎች ከመስራት እና ከግንዛቤ አንጻር ውስንነቶች መኖሩን ያስታወቁት አቶ ጌታሁን የአመራርና የዘርፋ ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ፈጥረው በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
በዞኑ 1ሺ 69 መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትና 6 የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች በማደራጀት በአጠቃላይ 1መቶ 60ሺ 824 አባላት ማፍራት መቻሉም አሳውቀዋል።
አቶ ጌታሁን አክለውም በዘርፉ የሚስተዋሉ የብድር አመላለስ፣ ተቋማቶቹ ኦዲት ማድረግ፣ የወለድ አልባ ቁጠባ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል።
ጥሩ መሻሻሎች እየታየበት ያለው የሴቶች ልማት ቡድን ትኩረት ሰጥቶ በመደገፍ ወደ ህብረት ስራ ማህበር ማሳደግ ይገባል ያሉ ሲሆን ያለ ኩፖን ግብአት በሚሸጡት አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አቶ ጌታሁን አሳስበዋል።
የመምርያው የልማት እቅድ ባለሙያ አቶ ዮናስ ሀብቴ የ6ወር ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሳወቁት በአገዳ ሰብል፣ በጥራጥሬ፣በአትክልትና በሌሎች ሰብሎች 4 ነጥብ 605 ቶን ምርት ለገበያ ቀርቧል ብለዋል።
አቶ ግምባሩ የአግኖት ዩኒየን ስራ አስከያጅ ሲሆኑ በዘርፉ ከ65 ፐርሰንት በላይ ሴቶች የስራ እድል ፈጠሯል ያሉ ሲሆን የወለድ አልባ ቁጠባ አገልግሎት ጉዳይ ግን ለዘርፉ ፈተና እየሆነ መሆኑን አሳውቀዋል።
አቶ ትዕግስቱ ተኸልቁ እና አቶ በህሩ ኑርሰፉ በውይይቱ የተሳተፉ አካላት ሲሆኑ በዘርፉ የሚስተዋለው የሰው ሀይል እጥረት፣ ህገ ወጥ ደላሎች መበራከት እና የማዳበርያ ብድር አመላለስ ችግር እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመላክቷል።
በመጨረሻም በመምርያው የግብይትና ምርት ግብአት ስራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ መሀመድ ሂያር አቅራቢነት በማዳበርያ ስርጭትና ግብይት ዙርያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና ተሰጥቷዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx