ጅራ ባንክ የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በወልቂጤ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የዘይትና የፉርኖ ዱቄት ድጋፍ አደረገ።

ጅራ ባንክ የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በወልቂጤ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የዘይትና የፉርኖ ዱቄት ድጋፍ አደረገ።

ሂጅራ ባንክ ስራ ከጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆን በተለያዩ ጊዜያት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች እየደገፈ እንደሚገኝ በሂጅራ ባንክ የወልቂጤ ከተማ ቅርንጫፍ አስታወቀ።

በወልቂጤ ከተማ የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኖ በርታ እንዳሉት በዛሬ ዕለት ባንኩ ለ70 የሚሆኑ አቅመ ደካሞችና ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ወገኖችን መጪዉ የረመዳን ጾም ፍቺ ወቅት እንዳይቸገሩ በማሰብ የዘይትና ዱቄት ድጋፍ ተደርጓል።

ባንኩ በመላዉ ሀገሪቱ 85 ቅርንጫፎች ከፍቶ አገልግሎቱን ተደራሽ ለመሆን እየተሰራ እንደሆነም የገለጹት አቶ ዲኖ በርታ በዛሬዉ እለት በወልቂጤ ከተማ ረቢ መስጂድ የተጀመረው ድጋፍ በቀጣይ በሌሎችም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ባንኩ የበለጠ አቅሙን ሲያሳደግ ለምስኪኖች የተሻለ ነገር ለመደገፍ እንደሚሰራም አመላክተዉ የዘንድሮ የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ ለሚስኪኖች በመቱ ፣ በአጋሮ ፣በነቀምት በሂጅራ ባንክ ቅርጫፎች በኩል ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነም አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ ከወለድ ነጻ ባንክ መቆጠብ እንዳለበትም አሰረድተዉ ወደፊት ባንኩ የበለጠ ተደራሽ እንደሚሆንም አሰታዉቀዋል።

የሂጅራ ባንክ ሰራተኛ አቶ ተባረክ ኑረዲን በበኩላቸዉ ባንኩ ሲመሰረት ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲኖር ለማድረግ የተመሰረተ እንደሆነ ተናግረዋል።

ኢስላሚክ ባንኮች ምስኪኖችን በመደገፍ ዘካ በማዉጣት የበኩላቸዉን እየተወጡ እንደሆነም አመላክተዉ በዘንድሮ የረመዳን ጾም ፍቺ ምክንያት በማድረግ ሂጅራ ባንክ የዱቄትና ዘይት ለተቸገሩ ዘገኖች ድጋፍ ማድረጉም ተናግረዉ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነም ጠቁመዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸዉ መካከል ወይዘሮ ሙሪዳ ሳዲቅ እና ወይዘሮ ከዲቻ ተማም እንዳሉት የተደረገላቸዉ ድጋፍ በዓሉን ያለምንም ጭንቀት እንድናከብር ያስችለናል ብለዋል።

ባንኩ ላደረገላቸዉ የዱቄትና የዘይት ድጋፍ አመስግነዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *