የ98 ዓመት እድሜ ባለፀጋዋ እናት ረጅም እድሜን ያስመኘ በጎ ተግባር በሶዶ ወረዳ ወጣቶች መፈፀሙን ተገለፀ።

በሶዶ ወረዳ ጊሚሴ ቀበሌ በላሊ ጊሲላ ማሪያም ቤተክርስቲያን ግቢ የሚኖሩ የ98 ዓመት እድሜ ላላቸው እናት የአዲስ ቤት ስርቶ የማስረከብና የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል።

የሶዶ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው ስዩም በሰናይ ተግባሩ ተግኝተው ለእድሜ ባለፀጋዋ እናት ቤት ከወረዳው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር እየሠሩ እንደደሚገኙ በመግለጽ ይህ በዚህ ክረምት ከተሰሩ 8ኛው ቤት እንደሆነ፣ በርካታ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ በወረዳችን ያሉ አቅመ ደካማ ወገኖች ችግር የማቅለል ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በወረዳው ያሉት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በሙሉ ለመድረስ አቅም እንደሌለ በመጠቆም በየቀበሌው እየተኬደ አርአያነት ያላቸው ተግባራት የምናሳየው ህብረተሰባችን ቆየት ያለው የመረዳዳት ባህሉን ወጥትነት ባለው መልኩ በየአቅራቢያው በባሰ ችግር ውስጥ ያሉትን ወገኖች ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል ወኔ ለመቀስቀስና ለማቀጣጠል እንደሆነ ነው ኃላፊው የተናገሩት።

የሶዶ ወረዳ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ግዛቸው ግርማ እንደተናገሩት የወጣቶች አደረጃጀት ከወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ጋር በመተባበር በየቀበሌው ቢያንስ አንድ የቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ለመርዳት፣ ቤት ለሌላቸው ቤት በመስራት መሰል በማስቀጠል አቅም ያለው ሁሉ ባለው ነገር አቅመ ደካማን በጉልበት፤ በቁሳቁስና በገንዘብ እንዲያግዝ የማስቻል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ለበጎ ተግባር የሚውሉት የፋይናንስና የቁሳቁስ እርዳታው ከወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጋር በመተባበር ከበጎ ፈቃደኞች በማሰባሠብ ከቲሸርትና ሌሎች የገቢ ማስገኛ አማራጮችን በመጠቀም እስከዛሬ ለተሰሩት 6ቤቶች አስፈላጊው ግብዓቶች እና ሌሎች የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፎች ማግኘት መቻላቸውን የወጣት ሠብሳቢው አስረድተዋል።

እንዲህ አይነት በጎ ተግባር በምድርም በሰማይም ዋጋ ያለው እንደሆነ የተናገረው የጊሚሴ ቀበሌ ወጣቶች አደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪ ወጣት ክብነህ ክስማሮ አቅመ ደካሞችን የማገዙን ተግባር ከተባበርንና ህብረተሰቡን ካስተባበርን ከዚህ በላይ መስራት እንችላለን ዛሬ በዚህ ደረጃ የደረሰውን የእናታችን ቤት ቀሪ ሥራው በማጠናቀቅ በአጭር ቀን እንዲገለገሉበት እንደሚያደረጉት ነው ቃል የገባው።

የአዲስ ቤት፣ የፍራሽ፣ የአንሶላ፣ የብርድ ልብስ ድጋፍ የተደረገላቸው የ98 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ ወ/ሮ አበበች ጋሻዬ በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ መደሰታቸው በምርቃት ስሜታቸውን በመግለጽ ድጋፉ ረጅም እድሜ ለመኖር እናዳስመኛቸው መናገራቸውን የመረጃው ያደረሰን የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *