የ2016 ዓ.ም የበጋ ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያና የክረምት መክፈቻ መርሃ ግብር በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ሀዋሪያት ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።


የ2016 ዓ.ም የበጋ ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያና የክረምት መክፈቻ መርሃ ግብር በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ሀዋሪያት ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን በመክፈቻ ንግግራቸው የዞኑ ማህበረሰብ የቆየ የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴቶችን በመጠቀምና ወጣቶችን በማሳተፍ ለአቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች አዲስ ቤት የመገንባት፣ የማደስና የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ በርካታ ስራዎችን በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችላል ብለዋል።

በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ12 ዘርፎች 107 ሺህ 74 ወጣቶችን በማሳተፍ 307 ሺህ 2 መቶ 33 የማህበረሰብ ክፍሎችን ማስጠቀም መቻሉን ተገልጿል።

በዚህም ከመንግስት ይወጣ የነበረው ከ88 ሚሊዮን 908 ሺህ 7 መቶ ብር በላይ ማዳን ተችላል ።

በበጋ ወቅት ወጣቶችንና የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የተከናወኑ ተግባራት በክረምትም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ፣ የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ተገኝተዋ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *