የ2014 ዓመተ ምህረት የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ከአቶ ክፍሌ ለማ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡-

የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤የተወደዳችሁ መላው የዞናችን ህዝቦች

እንኳን ለ2014 አዲሱ ዓመት በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

አዲሱ ዓመት የብርሃን ወጋገን፣ የአዲስ ተስፋ ጅማሮ፣ የሰላም፣የፍቅር፣ከአሮጌው ወደ አዲሱ የምንሻገርበት፣ አዲስ ተስፋ ሰንቀን ወደ ብልጽግና የምንሻገርበት ይሁንልን::

እንደሚታወቀው አዲስ ዓመት ሲመጣ ሰው ሁሉ በአዲስ ተስፋ ተሞልቶ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር መልካም ምኞቱን ይለዋወጣል።

አብሮ የመብላት የመጠጣት የወንድማማችነት ኢትዮጵያዊ ልምዳችን የሚያጠናክርበት ስለሆነ አሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታችን አንድነታችንና ጥንካሬያችን የሚገለፅበት ነው።

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን የጀመርነውን የለውጥና የብልፅግ ጉዞ እንድናስቀጥል ብሎም የሕዝባችንን ችግር ደረጃ በደረጃ እየለየን እንድንፈታ ከምንግዜውም በተለየ መልኩ የለውጥ ሀሳብን በማመንጨትና በመተግበር አጠቃላይ የዞናችን ህዝብ በማሳተፍ በጋራ መስራት ይኖርብናል።

የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የሀገራችን የጸጥታ ሀይሎች የሚያደርጉት የሀገራችን ሉአላዊነትና ነጻነት ለማስከበር የህልውና ዘመቻ ስኬታማ እንዲሆን የህዝባችን ድጋፍ ተጠናክሮ ድል የምናደርግበት እና አሸባሪው የህወሃት ሃይል ግብአት-መሬት የሚፈፀሚበት ዓመት ይሁንልን።

ለዚህም መላው የዞናችን ህዝቦች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ደጀንነትን ለመግለጽና አሸባሪው ህወሓት ጁንታ ቡድን ለማውገዝ በሰልፍ በገንዘብ በቁሳቁስ ልጁን መርቆ ወደ ግንባር በመሸኘት ስላበረከተው አስተዋፅኦ በዞኑ ህዝብና ብልፅግና ፖርቲ ስም ያለኝን ምስጋና እና አክብሮት ላቅ ያለ ነው።

ደካማ ኢትዮጵያን ማየት ዓላማቸው ያደረጉት ምዕራባዊያንና ህወሓት ህጻናትን በጦር ሲያማግድ፣ የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ወደ ጎን በመተው ቡድኑ በአማራና በአፋር ወረራውን በማስፋፋት ንጹሀንን ዜጌች ሲጨፈጭፍና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲፈጽም አለማውገዛቸው ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ የተላከላቸውን ሰብአዊ እርዳታ ለእብሪተኛው የትህነግ ሠራዊት በማደል ህዝቡን ለከፋ ጉዳት እየዳረጉ መሆናቸውን እያዩ ዝምታን መርጠዋል።

ይህም ለኢትዮጵያ ያላቸውን ጥላቻ እና ኢ-ሚዛናዊ አተያይ ያሳየ ነው።

እኛ ኢትዮጵያዊን እንደተለመደው በአንድነት በመቆም የውስጥና የውጪ ጠላቶች እያሳደሩብን ያለው ጫና ተቋቁመን በቅርቡ በድል እንወጣዋለን።

ሰላም ወዳድና ለውጥ ናፋቂው ህዝብ ፓርቲያችን ለመሰራት ያቀዳቸው በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ የጀመራቸዉን የብልጽግና ጉዞ አጠናክሮ እንዲሰራ እያደረገው ላለው ተሳትፎና አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ ፡፡

በመጨረሻም ለመላው የዞናችንና የሀገራችን ህዝቦች አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅረ፣የጤና፣የመቻቻልና አንንድነት እንዲሁም የብልጽግና አመት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በደረጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፡፡

    መልካም አዲስ ዓመት አመሰግናለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *