የፋይናንስ ዘርፉ በማጠናከር ሀብት የመፍጠርና የገቢ አሰባሰብ ስራን ይበልጥ እንዲሻሻል ሴክተር መስሪያ ቤቱ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አስታወቀ።

በግማሽ አመቱ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ንብረቶች በማስወገድ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ገቢ በማድረግ ሀብት የመፍጠር ስራዎች ላይ እየሰራ እንደነበር መምሪያው ገልጿል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2016 ዓ.ም የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን እንደተናገሩት በግማሽ ዓመቱ ሰፊ ጊዜ በመውሰድ ለ4ቱ መዋቅሮች የሀብት ክፍፍል ሲደረግ መቆየቱንና በጀቶችን ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ክፍያዎችን መከፈላቸው አስገንዝበዋል።

በቀጣይ የኦዲት ግኝት ተደራሽነትን በማስፋት፣ሰነዶች ኦዲት ተደርገው ግኝቶች ማስመለስ፣የሀብት ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ አብዶ በዘርፉ ያልተከናወኑና ያጋጠሙ ችግሮች ለይቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል አቶ አብዶ።

የፋይናንስ ዘርፉ ለማጠናከር ሀብት በመፍጠርና የገቢ አሰባሰብ ስራን ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስታውቀዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በመምሪያው በግማሽ አመቱ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ንብረቶች በማስወገድ ከ5 መቶ 33ሺ 624 ብር በላይ የተገኘ ሲሆን በሁሉም መዋቅሮች መሰል አይነት ሀብት የመፍጠር ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ምክትል ኃላፊና የመንግስት ፋይናንስ አስተባባሪ አቶ ሳሊም ሸምሱ በበኩላቸው በዘርፉ የሚገጥሙ የጥሬ ገንዘብ እጥረቶች እና ሌሎች ችግሮች ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ለአብነትም ደረሰኞች በክልል ደረጃ እየታተሙ መሆኑ አመላክተዋል።

የተጀማመሩ ልማቶችን ለማስቀጠል ከተራዶ ደርጅቶች ተቀናጅቶ መስራት ያሉንን ሀብቶች፣ጥሬ ገንዘቦችንና ነዳጅ በአግባቡ በመጠቀ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ሳሊም አክለውም በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት ለማምጣት የፋይናንስ፣የገቢ ተቋምና ተራዶ ድርጅቶች ተቀናጅተው መስራት አለባቸው ነው ያሉት።

በመምሪያው የሲቪክ ትብብር አስተባባሪ አቶ ቴድሮስ አለሙ በበኩላቸው በዞኑ ያሉ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ባሉበት አካባቢ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ሲሆን መንግስት የገጠመው የበጀት እጥረት በመቅረፍ በርካታ የልማት ስራዎች የሚያከናውኑ በመሆናቸው ትኩረት ተሰጥቶ እንዲደገፉ ሲሉ ተናግረዋል።

በውይይቱ የተገኙ አካላት እንዳሉት የኦዲት ግኝት ከማድረግ፣ደረሰኞች ወጪ ከሆኑ በኋላ በወቅቱ ተመላሽ አለመደረጋቸው በጥብቅ ከመከታተል፣ገቢን አሟጦ ከመጠቀም አንጻር ለዘርፉ ችግር እየሆኑ ያሉ ጉዳዮች መሆናቸው አንስተዋል።

በቀጣይ የፋይናንስ ዘርፉ ለማጠናከር የሀብት አጠቃቀምና የገቢ አሰባሰብ በአጠቃላይ በዘርፉ የሚገጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎች በወቅቱ እንዲጠናቀቁ በአጽንኦት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል

በመድረኩም የመመሪያው ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አካላት፣ከየመዋቅሩ የመጡ የፋይናንስና የገቢ ኃላፊዎች፣ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *