የጸጥታዉ መዋቅር በማጠናከር በዘርፍ የበለጠ ዉጤታማ ስራ ለመስራት የፖሊስ አባሉ መገምገምና ማህበረሰቡን ያሳተፈ ወንጀል የመከላከሉ ስራ አጠናክሮ እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።

ሰየጸጥታዉ መዋቅር በማጠናከር በዘርፍ የበለጠ ዉጤታማ ስራ ለመስራት የፖሊስ አባሉ መገምገምና ማህበረሰቡን ያሳተፈ ወንጀል የመከላከሉ ስራ አጠናክሮ እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።

የፖሊስ ኃይሉ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ ለማጠናከር ከየወረዳዉና ከተማ አስተዳድር የተዉጣጡ የሰላምና ጸጥታ ላፊዎች ፣የሚሊሻ ጽህፈት ቤትና የፖሊስ አዛዦችና ሌሎች የሚመለከታቸዉ ባለ ድርሻ አካላቶች በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ዉይይት ተካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ በጸጥታ ዘርፍ ላይ ሪፎርም እየተደረገ ሲሆን የልዩ ሀይል የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ ፖሊስና ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅር አደረጃጀት ዉስጥ ገብተዋል።

የአካባቢዉ ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ረገድ በመደበኛ ፖሊስ አባላት ላይ ትልቅ ሀላፊነት የወደቀ ሲሆን የመደበኛ ፖሊስ ሪፎርም ለማድረግና በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸዉ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ተግባቦት ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነም አብራርተዋል።

የፖሊስ የሪፎርሙ ስራ በዋናነት በሁለት ጉዳዮች ዙሪያ ሲሆን በመጀመሪያ ከዞን ጀምሮ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ የፖሊስ ቁመናና ለማህበረሰቡ እየሰጡ ያሉትን ግልጋሎት የሚፈተሽበትና የፖሊስ አባላቱ ሂስ ግለ ሂስ ካደረገ በኃላ መልሶ የማደራጀት ስራ እንደሚሰራም አብራርተዋል።

የሪፎርሙ ሰራ አሁን ባለቸዉ ብቃትና አጠቃላይ ተነሳሽነታቸዉ መነሻ በማድረግ መልሶ የማደራጀቱ ስራ ይሰራል ያሉት አቶ አብድልሀፊዝ በየአካባቢዎች ላይ ይህንን አደራጅተዉ ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ መሪዎች የመፍጠር ስራም እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የፖሊስ ሀይል ወደ ነበረበት ቁመና እንዲመለስ በትኩረት እንደሚሰራም አብራርተዉ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸዉ የመልካም አስተዳድርና የሰላም እጦት ጥያቄዎች ምላሽ የሚመልስ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።

የፖሊስ ተግባር በዋናነት ወንጀል መከላከልና ወንጀል ከተፈጠረ በኋላ አጠቃላይ በምርመራ አጣርቶ ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረጉ ስራም ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽዕኖት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አብራርተዋል።

ማህበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ወንጀል ልርተዉ የሚሸሸጉ አካላት አሳልፎ ለህግ የመስጠትና የአካባቢዉን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ በበኩላቸዉ በዞኑ እየታየ ያለዉን አንጻራዊ ሰላም መምጣት የፖሊስና የማህበረሰቡ ሚና የጎላ እንደነበረና በዘርፉ የተሻለ ዉጤት እንዲመጣ በርካታ ስራዎች መሰራቱም አመላክተዋል።

ይህ ዉጤት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የጸጥታ አባላቱና አመራሩ መገምገሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ የየወረዳና ከተማ አስተዳድር የጸጥታና የፖሊስ ሀላፊዎች በተገኙበት በሰነዱ ላይ ዉይይት ተደርጓል ብለዋል።

የፖሊስ አባሉ ቀደም ሲል የነበረበት ቁመና መፈተሽ አለበት የሚል አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዉ የሚሰራ ፖሊስ እንዳለ ሁሉ ችግር የሚፈጥር ፖሊስ እንዳለም የተገመገመበት ሁኔታ መኖሩንም አመላክተዋል።

አካላዊ ግምገማ ሲካሄድ የፖሊስ ረካላት በርካታ ችግሮች ዉስጥ እንዳለም የተገመገመበት ሂደት መኖሩም አመላክተዉ ይህንንም ችግር ለይቶ ለማዉጣት አጠቃላይ የፖሊስ አባሉ የሂስ ግለሂስ በማድረግና በሂስ ግለሂስ ያላለፈ የፖሊስ አባል ፖሊስ ሆኖ መቀጠል እንደማይችልም ተናግረዋል።

የጸጥታዉ መዋቅር በማጠናከር በዘርፍ የበለጠ ዉጤታማ ስራ ለመስራት ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ መስራት እንደሚገባም አብራርተዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለ ድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት ትልቅ አቅም ያላቸዉ መርማሪ ፖሊሶች ለማፍራትና ለማጠናከር ተገቢነት ያለዉ ስልጠና መስጠት ይገባል ብለዉ በዚህ ዘርፍ በደንብ ገምግሞ ማስተካከል እንደሚገባም አብራርተዋል።

ከወንጀለኛ ጋር የሚያብር የፖሊስ አባል በተገቢዉ መገምገምና ማጣራት እንደሚገባም አመላክተዉ ጠንካራና በዘርፉ ዉጤታማ ስራ መስራት የሚችል የፖሊስ አባል በማደራጀት የአካባቢዉን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ወቅቱን የጠበቀና ቀጣይ በሚሰሯቸዉ ስራዎች የተሻለና ዉጤታማ ስራ መስራት የሚያስችላቸዉ መድረክ መሆኑም ጠቁመዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዘን ኒንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *