የጥምቀት በዓል አከባበር ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት ተገለጸ።

ጥር 9/2015 ዓ ም

የጥምቀት በዓል አከባበር ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት ተገለጸ።

የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡

የዘንድሮ የጥምቀት በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከዝግጅት ምዕራፍ እስከ ማጠቃለያዉ ድረስ እቅድ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን በዚህም ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት መደረጉን የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛኝ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ገልጸዋል ።

በክርስትና እምነት ተክታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ ክበረ በዓለት አንዱ የጥምቀት በዓል ነዉ ያሉት ኮማንደር ጠጄ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በዞኑ በሚገኙ በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅሩ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተሰርቷል።

የስጋት ቀጠና አካባቢዎች በመለየትና የእምነቱ ተከታዮች ያለምንም የጸጥታ ችግር በዓሉ በሰላም አክብረዉ ወደ ቤታቸዉ እንዲመለሱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ኮማንደር ጠጄ ተናግረዋል።

ሰላም የማስከበሩ ስራዎች እንዲሠሩ ለጸጥታ አካላቱ ስምሪት መሰጠቱን ገልጸዉ ህዝባዊ አደረጃጀት ፣ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና ሌሎችም የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ስምሪት መሰጠቱንም አብራርተዋል ።

የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ እንዲከበርና በሰላም ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ካለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የትኛውም ህዝባዊ በዓላት በሰላም ማክበር እንደማይቻል ሁሉ ህብረተሰቡ ከፀጥታው አካል ጎን በመሆን የተለመደውን ትብብር እንዳያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ህብረተሰቡ የጸጥታ ስጋት እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ጥቆማ በመስጠት የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *