የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሻሻል እየተከናወኑ የሚገኙ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ ።


መምሪያው በዞኑ የተመረጡ ወረዳዎች በወረዳ ትራንስፎርሜሽን ሞዴል ለማድረግ የንቅናቄ መድረክ በቡታጅራ ከተማ አካሄደ።

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን የንቅናቄው መድረክ በተካሄደበት ወቅት እንደተናገሩት በዞኑ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን ትግበራን በማጠናከር ጥራቱን የጠበቀ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው::

በወረዳ ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የሞዴል ቀበሌዎች አፈጻጸም 85% ሆኖ በዚህም 85% በላይ ሞዴል ቤተሰቦች፣ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የሆኑ ቀበሌዎች፣ ቤት ውስጥ ከመውለድ ነፃ የሆኑ፣ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በጤና ሞዴል የሆኑ፣ ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸው የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃዶችን የተፈጠሩበት እና የማሕበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ሽፋን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ማድረግ በዕቅዱ ከተያዙ መለኪያዎች እንደሚገኙበት አቶ ሸምሱ አብራርተዋል፡፡

የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ የህብረተሰቡ ጤና በማጎልበት እረገድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሀገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለመድሃኒት የምታወጣው ወጪ ለመቀነስ ያስችላል።

ይህ ደግሞ ተጨማሪ የልማት ስራዎች በመስራት ህብረተሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ኃላፊው አብራርተዋል።

የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳውን ለማሳካት ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ሲሆን ባለድርሻ አካላትም የጤናው ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ከተቋሙ ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ አቶ ሸምሱ አሳስበዋል።

በመምሪያው የልማት እቅድ ኢኮኖሚ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ በስር በበኩላቸው ከትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አንዱ ሞዴል ወረዳ መፍጠር ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ወረዳዎች በመለየት ሞዴል ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

እንደ አቶ ታደሰ ገለፃ የወረዳ ትራንስፎርሜሽኑን ዕቅዱን በዞኑ በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች መተግበር እንዲቻል በተያዘው በጀት አመት ሰባት የተመረጡ ወረዳዎች ሞዴል በማድረግ በቀጣይ ከወረዳዎቹ የተገኙ ተሞክሮዎች በፍጥነት ወደ ሌሎች ወረዳዎች ለማስፋት ታቅዷል።

በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች ሞዴል በማድረግ አምራች፣ ጤናውን የተጠበቀ የነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል ዳይሬክተሩ።

የንቅናቄው መድረክ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የጤና ተግባራት በተቋሙ ጥረት ቢቻል የማይሳኩ በመሆናቸው በቀጣይ ከጤና ተቋም ጋር በመሆን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

አያይዘውም ተሳታፊዎቹ በወረዳዎቻቸው ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በተያዘው በጀት አመት ሞዴል በማድረግ ተሞክሮዎችን ለማስፋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *