የጤና ተቋማት ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የህበረተሰቡ ጤና እንዲጎለብት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡


በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች በማስቀጠተል ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽዎች ለመከላከል እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት ተግባር አፈጻጸም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ እንደገለፁት የጤና ኤክስቴንሽ ፕሮግራም ውጤታማ ለማድረግ የባለሙያዎቹ አቅም ከማሳደግ በተጨማሪ እየተስፋፉ የሚመጡ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በመከላከል አምራችና ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ ለማፍራ የጤና ተቋማት የላቀ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ የተቀመጡ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች የህብረተሰቡ ጤና ለማጎልበት ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አቶ አሸናፊ አስገንዝበዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ የወባ በሽታ የሚያስከትለው ጫና ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለማስቀጠል እና በሽታውን አስቀድሞ መከላከል እንዲችል ህብረተሰቡ ያሳተፈ የመከላከል ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጤና ተቋማት በሰው ሀይልና በቁሳቁስ በማሟላት ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በወሊድ ወቅት የሚፈጠር የእናቶች ሞት የሚያስከትለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ የጤና ተቋማት ወቅቱን የሚመጥን የወሊድ አገልግሎት እና የተጠናከር የተቋማት ትስስር በመፍጠር የእናቶች ህይወት ለመታደግ በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ የጤና ተቋማት ግንባታ ለማጠናቀቅ ባለሀብቶች እና ማህበረሰቡ ማሳተፍ ይገባል ያሉት ም/አስተዳዳው ተቋማቱ በቁሳቁስ በማሟላት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በበኩላቸው የእናቶችና ህፃናት ሞት በመቀነስ ጤናቸው ለማጎልበት መምሪያው እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በጤና ተቋማት የሚገነቡ የእናቶች ማረፊያ ለእናቶች ምቹና መሰረታዊ ፍላጎታቸው ያሟሉ እንዲሆኑ እየተሰራ በመሆኑ በተቋማቱ በሰለጠነ የጤና ባለሙያዎች የሚወልዱ እናቶ ቁጥር በየጊዜው እያደገ ይገኛል፡፡

ይህ ደግሞ በወሊድ ምክንያት የሚሞቱ እናቶች ህይወት ለመታደግ የሚያስችል በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ የማህፀን ወደ ውጭ መውጣት ችግር የገጠማቸው እናቶች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉንም አውስተዋል፡፡

በቀጣይ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሐዊ በማድረግ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል በትኩረት አንደሚሰራ ተጠቁሟል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በጤናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ሲሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኃላፊው ገልጣል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የጠየና ጽ/ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ባለሙያዎችና አጋ ድርጅቶች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *