የጎዳና ላይ ሩጫዎች ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ በአለም ደረጃ የበለጠ ውጤታማ እንድትሆን የጎላ ሚና እንዳላቸው ኢፌድሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።

በቡታጅራ ከተማ የኬሮድ የ1ዐ ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደዋል።

የኢፌድሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስተር የስፖርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እንደገለፁት የጉራጌ ህዝብ በስራ ወዳጅነቱ ኢትዮጵያን ያስተማረና ኢኮኖሚውን እንዲያድግ ያደረገ ነው።

በስፖርቱም ዘርፍ አንጋፋ አትሌቶች በማፍራት የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረጉ አትሌቶችም በማፍራት ዞኑ ታሪካዊ ስራዎችን ማበርከቱ ተናግሯል።

የጎዳ የሩጫ ውድድሮች መዘጋጀታቸው ቀጣይ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ብላቱ እንደገለፁት የተደረገው ሩጫ ውድድር የአለም አትሌቲክስ ሻፒዮና በሚደረግበት ወቅት በመሆኑና ኢትዩጵያ በአለም በ2ኛ ደረጃ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆና እየመራች ባለችበት ወቅት በመሆኑ ለየት ያደርገዋል።

ስፖርት ጤናማ ዜጋ እንዲፈጠር ያደርጋል ያሉት አቶ ተስፋዬ ወጣቶች በስፖርቱ ያላቸው አመለካከትና ተሳትፎ በማሳደግ በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ አትሌቲክስ ዘርፍ ለማዘመን በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ተተኪ አትሌቶችን ለማፋራት ሀገራችንን ዛሬም በአለም አደባባይ ባንዲራዋ ከፍ ለማድረግ የዞኑ መንግስት የበኩሉን ይወጣል።

በዞኑ በአትሌቲክስ ዘርፍ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት በፕሮጀክቶች በአካዳሚዎችና በክለቦች በመታቀፍ፣ በስፖርታዊ ጨዋነት ተገቢ ስልጠና በመውሰድ በዘርፉ የሚገኘው የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ አበራ የዘቢደር የአትሌቲክስ ክለብን ለአብነት ተጠቃሽ ነው ብለዋል ።

የቡታጀራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ነስሩ ጀማል በኬሮ ኦድ የልማትና ስፖርት ማህበር አዘጋጅነት በከተማው የተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተተኪ አትሌት ለማፍራት ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባሻገር የልዩነተ ሃሳቦችን በማጥበብ ዞናዊና ሃገራዊ የአንድነትና አብሮነት እሴቶቻች ለማጓልበት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ አለዉ ብለዋል።

የቡታጀራ ከተማ በእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁት ከንቲባው ቀጣይም በከተማው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሠማርተው እራሳቸውንና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ባለሀብቶችን ተቀብላ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

አትሌት ተሰማ መኮንን አትሌት ምትኩ አያሌና አትሌት ሀለፎም ተስፋዬ በጋራ በሰጡት ሀሳብ መሰል አይነት ውድድሮች መካሄዳቸው ልምድ ለማካበትና ቀጣይ በሀገርና በአለም አቀፍ ውድድሮች ብቁ ተወዳዳሪ እንድንሆን ይረዳናል ብለዋል።

ቀጣይም በዚህ ውድድር ያገኘነው ልምድና ብቃት በማሳደግ ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ ታዋቂና አሸናፊ እንድትሆን ጥረት እንደሚያደርጉ አስገንዝበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *