የግብርና ባለሙያዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና መልካም ተሞክሮዎችን ቀምረው በማስፋት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባቸወረ የእነሞርና ኤነር ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

በወረዳው ውስጥ በመደበኛና በበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት የተከናወኑ ተግባራት በግብርና ባለሙያዎችና በባለድርሻ አካላት ተጎብኝቷል፡፡

የእነሞርና ኤነር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የግብርና ጽ/ቤቱ ሐላፊና አቶ መብራቴ ተክሌ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በወረዳው ውስጥ የተከናወኑ የመደበኛና የበጋ መስኖ ስንዴ እና ሌሎችም መደበኛ የመስኖ ልማት ስራዎች አፈጻጸም በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

እንደ ሐላፊው ገለጻ የግብርና ባለሙያዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና መልካም ተሞክሮዎችን ቀምሮ በማስፋት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳውቀዋል፡፡

የበልግ እርሻና የተፋሰስ ልማት ስራ ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ እንደሚገኝ ያመላከቱት አቶ መብራቴ በቡና ልማት ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ምክትል ሐላፊና የተፈጥሮ ሐብት ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ከድር በበኩላቸው በወረዳው በተለይም በመስኖ ልማት ላይ ተደራጅው ወደ ተግባር በመግባት ተጠቃሚ ከሆኑ አርሶ አደሮችና ወጣቶች ልምድ በመውሰድ ወደ ሁሉም ቀበሌ ለማስፋትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በወረዳው በመስኖ ስራ ላይ ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር አብድል ማሊክ፣ ብርሃኑ፣ ወጣት ሳላዲን በድሩ፣ቃሲም አብዶ እና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት የባለሙያ ምክርና የአመራር ድጋፍ ተቀብለው የጓሮ አትክልትና በበጋ ሰንዴ በመስኖ በማልማት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት በተለይም ጥቅል ጎመን ለገበያ በማቅረብ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን አብራርተዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ በመንግስት በኩል ለተደረገላቸው የግብዓት ድጋፍ እና የአመራርና የባለሙያ እገዛ ምስጋናቸውን ማቅረባቸው ከወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በማሳ ጉብኝቱ ላይ ከተሳተፉ ባለሙያዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በመስኖ ልማት ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ያከናወኑት ተግባር አበረታችና አስተማሪ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ይህንን መልካም ተሞክሮ ወደ ተመደቡበት ቀበሌ አርሶ አደሮች በማስፋት ሙያዊ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *