የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ 11ኛ ዙር የግብርና አማካሪ ካውንስል ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጸጋዬ ተረፈ ክልሉ በእንሰት እምቅ አቅም መኖሩን ተከትሎ በዘርፉ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም የአርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የእንሰት በሽታ፣ ሂደትና ልማት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በግብርና ዘርፉ የተሻለ ስራ ለመስራት የምርምር ማዕከላት የግብርና ማነቆዎች ለመፍታት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ከእንሰሳት ዝርያ ማሻሻል ጋር ተያይዞ የናይትሮጅን ፈሳሽ እጥረት ለመፍታት በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ግብርና በዞኑ በግብርናው ዘርፍ የአርሶ አደሩ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎች መፍታት ይገባል።

ለዚህም የምርምር ማዕከላት በዘርፉ በቂ ምርምር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።

በዞኑ እንሰት የአርሶ አደሩ የምግብ ዋስት መሆኑን ተከትሎ ዝርያ፣ በሽታና አስፍቶ መስራት ላይ ሁሉም በዘርፉ በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

እንደ አቶ አበራ ገለጻ በእንሰሳት ዘርፍ በዞኑ እምቅ አቅም እንዳለ ገልጸው የፈሳሽ ናይትሮጂን ችግር ለመፍታት የክልሉ መንግስት በትኩረት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የአርሶ አደሩ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዞኑ የተጀመረው ስራ ይበልጥ አስፍቶ ለመስራት ሁሉም በዘርፉ ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት አቶ አበራ ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጅማ፣ የወራቤ፣ የአምቦ፣ የወልቂጤ የምርምር ማዕከላት በጋራ እንዳሉት በዞኑ በሰብሎች ላይ ያሉ የበሽታና የዝርያ ችግር ለመፍታት እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

በተለይም ይህንን ችግር ለመቀነስ በምርምር ማዕከላት ዝርያቸውን የተረጋገጡ የምርምር ውጤቶችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የጀመሩት ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በዞኑ በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውንና ይህም ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ይበልጥ አጠናክሮ መስራት ይኖርባቸዋል።

እንደ ሀገር ከተረጂነትና ልመና ለመላቀቅ በግብርናው ዘርፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸው ለዚህም የምርምር ማዕከላት በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በዞኑ የእንሰት፣ የቡናና ሌሎችም ሰብሎች ላይ የሚታዩ ማነቆዎች የምርምር ማዕከላት ተገቢውን ምርምር በማድረግ ችግሮቹ ለመፍታት መስራት ይኖርባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *