የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጊዜወርቅ አለሙ በሰጡት መግለጫ በ2016 በጀት አመት በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች የእሳት አደጋ መከሰቱን ገልጸው ለአብነትም በቸሀ ወረዳ 8 ቤቶች ተቃጥለው 82 ቤተሰቦች የእሳቱ አደጋ ተጋለጭ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጊዜወርቅ አለሙ በሰጡት መግለጫ በ2016 በጀት አመት በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች የእሳት አደጋ መከሰቱን ገልጸው ለአብነትም በቸሀ ወረዳ 8 ቤቶች ተቃጥለው 82 ቤተሰቦች የእሳቱ አደጋ ተጋለጭ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የቤቶች ጥግግት፣ በተዳፈነ እሳት ላይ ቤት ዘግቶ መሄድ፣ የደን መሬትን ወደ እርሻ ማሳ ለመለወጥ እሳት መልቀቅ፣ ያለ ጥንቃቄ ማር መሰብሰብና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ካለ ማድረግ የተነሳ የእሳት አደጋ እንደሚከሰት ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

የእሳት አደጋ ከተከሰተ በኃላ ከመከላከል ይልቅ የቅድመ መከላከል ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው ከሚከሰተው የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት መውደም መከላከል ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

ጽህፈት ቤቱ በዞኑ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደግ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ በርካታ ስራዎች ሲሰራ እና እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ የመተጋገዝና የመረዳዳት የዳበረ እሴቱ በመጠቀም ጽህፈት ቤቱ ቤትና ንብረት የወደመባቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን ቤት ከመስራት ባለፈ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ መደረጉንም አመላክተዋል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም በእሳት ከወደሙ ከ1መቶ አካባቢ ቤቶች 82 ቤቶች በመንግስት፤ በባለሀብት፤ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በማህበረሰቡ ቅንጅት መገንባት መቻሉን አንስተዋል።

በያዝነው በጀት አመት ገና የበጋው ወቅት ሳይጀምር በቀን 25/01/2017 ዓ. ም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በጌታ ወረዳ የእሳት አደጋ ተከስቶ አንድ ቤት መቃጠሉ ያመላከቱት ኃላፊዋ ለዚህም ህብረተሰቡ አሁንም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

አደጋው ለመቀነስና ለመከላከል ለማህብረሰቡ በትምህርት ቤቶች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የበለጠ ግንዝቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

One Comment:

  1. Your blog is a beacon of light in the often murky waters of online content. Your thoughtful analysis and insightful commentary never fail to leave a lasting impression. Keep up the amazing work!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *