የጉራጌ ዞን የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

ጥር 9 /2015 ዓ/ም

የጉራጌ ዞን የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

የዞኑ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክርቤት በተለያዩ ዞናዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይትም አካሄዷል::

በስብሰባ የብልፅግና ፖርቲ፣ ኢዜማ፣ አብን እና እናት ፖርቲ የተሳተፉ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሲሆን የጋራ ምክር ቤት ማጠናከር በየምርጫ ክልልሉ ያሉ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲጠናከሩ ድጋፍ ማድረግ፣ የጉራጌ ዞን ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ም/ቤት ውስጠ ደንብ ላይ ተወያቶ አጽድቋል። እንዲሁም በዞኑ ሰላም ጉዳይ ላይ ምክክር አደርገዋል::

በዞኑ የሚንቀሳቀሱ ፖርቲዎች በጋራ ምክር ቤት ያፀደቁት የቃል-ኪዳን ሰነድ መነሻ በማድረግ የሚያደርጉት ግንኙነት መጠናከር እንዳለበት በዛሬው እለት የገመገሙ ሲሆን በቀጣይ የጋራ ምክክሩ በማጠናከር የዞኑ የሰላምና ልማት በማስቀጠል ማህበረሰቡን የበለጠ ተጠቃሚ የሚሆንበት ተግባር መፈፀም እንደሚገባ በፖርቲዎቹ መግባባት ላይ ተደርሷል::

የም/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ በንባብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን የፖለቲካ ፖርቲዎቹ የስምምነት ውል ተፈራርመዋል::

በተጨማሪም በስብሰባው በውስጠደንቡ መሰረት ም/ቤቱን የሚያጠናክሩ ሁለት የተለያየዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ተደራጅተዋል::

የዞኑ የሰላምና መረጋጋት ጉዳይ የሁሉም የፖለቲካ ፖርቲዎች ጉዳይ በማድረግ ከአባሎቻቸው ጋር መምከር እንደሚገባቸውና በዞኑ ውስጥ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲታረሙ በተለይም በፖርቲ አባላት ምንም አይነት ህገወጥ-ተግባር ላይ ተሳታፊ እንዳይሆኑ ሁሉም ፖርቲዎች መስራት እንዳለባቸው ተስማምተዋል።

ዞኑ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር የዞኑ ህዝብ በልማት ስራ ላይ እንዲያተኩር የሁሉም ፓርቲ እገዛ ማድረግ እንደሚገባ የም/ቤቱ አባላት ከስምምነት ደርሰዋል::

በጋራ ምክር ቤቱ ሁሉም የፖለቲካ ፖርቲዎች ሁለት ሁለት ተሳታፊ ያላቸው ሲሆን በውይይት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ ከኢዜማ እና የም/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ መሠለ ጫካን ከብልጽግና ጨምሮ ከሁሉም የፓለቲካ ፓርቲ የጋራ ም/ቤት አባላት ተገኝተዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *