የጉራጌ ዞን የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረሃይል የእስካሁኑ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ ገምግማል።

የህዝብ ሀብትና ንብረት ለታለመለት አላማ እንዳይውል በመዋቅሮችና ግለሰዎች የሚስተዋለውን የኦዲት ግኝት ማስመለስ ላይ ግብረ ሃይሉ ይበልጥ በተጠናከረ መንገድ መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ልክነሽ ስርገማ በግምገማው ወቅት እንዳሉት የህዝብ ሀብትና ንብረት ለታለመለት አላማ እንዳይውል በመዋቅሮችና ግለሰዎች የሚስተዋለውን የኦዲት ግኝት ለማስመለስ ግብረ ሃይሉ በተጠናከረ መንገድ መስራት ይጠበቅበታል።

በበጀት አመቱ 97 ሚሊዮን 136ሺህ 319 ብር ለማስመለስ ታቅዶ ግብረ ኃይሉ በደረገው ቅንጅታዊ ርብርብ 76 ሚሊዮን 619 ሺህ 162 ብር ማስመለስ ተችላል ብለዋል።

በዘርፉ ግብረሃይሉና ምክር ቤቱ የተጠናከረ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን መሰራቱ ያነሱት ክብርት አፈ ጉባኤዋ በዚህም ከባለፊት ጌዜአት ጋር ሲነጻጸር ለውጦችን መታተቱን አንስተዋል።

በቀጣይም በዘርፉ የበለጠ በመስራት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እቅድ በማቀድ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

በዘንድሮ አመት ከሌላ ጊዜ በተሻለ መልኩ በርካታ ግኝቶችን በማስመለስ ወደ መንግስት ካዝና ማስመለስ መቻሉን ጠቁመው በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ስራ ለመስራት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ተጠናክሮ እንደሚቀጠል ጠቁመዋል።

ከአፈር ማዳበሪያ 40 ሚሊዮን 277 ሺህ 708 ብርና ከጥሬ ገንዘብ ጉድለት 20 ሚሊዮን 398 ሺህ 876 ብር ማስመለስ መቻሉንም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበጀት አመቱ የባከኑ ውዝፍ የህዝብና የመንግስት ሀብት ለማስመለስ የተሰራው ስራ ማጠናከር ይገባል።

በቀጣይ በዘርፉ የሚታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ ይበልጥ ውጤታማ ስራ ተቀናጅተውና ተናበው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *