የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የሁለት አመት ከግማሽ የመሰረታዊ ድርጅት የአባላት የማጠቃለያ ኮንፈረንስ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ኮንፈረንስ “ከእዳ ወደ ምንዳ በአባላት ተሳትፎ” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በኮንፈረንሱ ላይ እንዳሉት ፓርቲው በምርጫ ወቅት ለህዝብ የገባቸውን ቃሎች ላይ እስካሁን የተከናወኑና ያልተከናወኑ ተግባራት በመለየት አባሉ የተግባር አንድነት በመያዝ በቀጣይ ምላሽ ለመስጠት አባሉ መትጋት ይኖርበታል።

በዞኑ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና ጸጥታ የተከናወኑ ተግባራቶችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ አባሉ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል ።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ በመክፈቻ ንግግራቸው የብልጽግና ጉዞና የሀገሪቷ ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲፋጠን አባሉ የአመለካከትና የተግባር አንድነት ጉድለቶችን በማረም ግንባር ቀደም ሚና መወጣት ይጠበቅባታል።

ፓርቲው በሁለት ዓመት ከግማሽ ጊዜ ቆይታው በርካታ ድሎችን ያስመዘገበ ቢሆንም ፈተናዎችንም ማሳለፉን አቶ ክብሩ ተናግረዋል።

በዚህም ፓርቲው ካከናወናቸው ተግባራት ተቋማዊ መሰረት ያለው የተሻለ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት እሴት ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሄራዊ አንድነት የመገንባት ስራ፣ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም እየተስተዋሉ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮችን የሀሳብ ልዩነትና አለመግባባት ለመፍታት እየተሰራ ያለው ስራና አካታች ህዝባዊ ውይይት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

በዞኑ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን የገለጹት አቶ ክብሩ ይህም አባሉ ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።

በዞኑ ከ160 ሺህ በላይ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ያሉ ሲሆን እነዚህም እንደ ዞን ፓርቲ ለመትከልና የመሪነት ሚናው ይበልጥ ከፍ እንዲል በተገቢው በመጠቀም የብልጽግና ጉዞ ህዝብ ባሳተፈ መልኩ እንዲጠናከር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኮንፈረንሱ አላማ የብልጽግና ፓርቲ በሁለት አመት ከግማሽ በልማትና በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና ጸጥታና በዴሞክራሲ ያከናወናቸው ተግባራቶችን ይበልጥ ለማስቀጠልና የነበሩ ጉድለቶችን በማረም ለመስራት መሆኑን ተገልጿል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ፓርቲው ብልጽግና በሁለት አመት ተኩል ያከናወናቸው የተሻሉ ተግባራትና ያጋጠሙ ፈተናዎችን መሰረት ያደረገ የውይይቱ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *