የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ በበኩላቸው ፓርቲው ባለፉት 3 አመታት ገጠሙት በርካታ ፈተናዎች በበሳል የአመራር ጥበብ በማለፍ በርካታ ውጤት ማስመዝገብ እንደቻለ ገልፀዋል።

ብልፀግና በአጭር ጊዜ በርካታ አስደማሚ ለውጦች ያስመዘገበ አካታችና የወድማማችነት እሴት እያጎለበተ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

በጉራጌ ዞን የዞን ማእከል የብልፅግና ፓርቲ ሙሁራን አባላት “ከፈተና ወደ ልዕልና እንቅፋት እንደ ድልድይ ተጠቅሞ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መንደርደር” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ኮንፈረንስ በወልቂጤ ከተማ አካሄደዋል።

በኮንፈረንሱ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለፁት ብልፀግና ፓርቲ በአጭር ጊዜ በርካታ ለውጦች ያስመዘገበ አካታች፣ የወድማማችነት እሴት እያጎለበተ የሚገኝ ፓርቲ ነው።

ፓርቲው ባለፋት 3 የለውጥ አመታት በርካታ ፈተናዎች የገጠሙት ቢሆንም መላው አባሉና ህዝቡ በማሳፍ የሀገር ህልውና በማስጠበቅ በርካታ አገራዊ ስኬቶች አስመዝግበዋል ብለዋል።

አቶ መሀመድ አክለውም በቀጣይ የሀገር ሉኣላዊነት እንዲሁም የዜጎች ደህንነት ማስጠበቅ የፓርቲው ዋና የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

አሁንም በየአካባቢው የዜጎች ሰላም የሚነሱ ሀይሎች መኖራቸው ገልፀው እነዚህ ሀይሎች የሁሉም ዜጎች ጠላት መሆናቸውን በመገንዘብ በጋራ ልንታገላቸው ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክፍሌ ለማ በበኩላቸው ፓርቲው ባለፉት 3 አመታት ገጠሙት በርካታ ፈተናዎች በበሳል የአመራር ጥበብ በማለፍ በርካታ ውጤት ማስመዝገብ እንደቻለ ገልፀዋል።

በተለይም የህወሃትና የተላላኪዎቹን ሀገር የማፍረስ ሴራ የፓርቲው አመራሮችና መላው አባላት እንዲሁም በመላው ህዝቦች የጋራ ትግል መክሸፉ አቶ ክፍሌ ተናግረዋል።

አቶ ክፍሌ አክለውም አሁንም እዚህም እዚያ ያላለቀላቸው የጋራ ጥረት የሚጠይቁ ችግሮች እንዳሉ ገልፀው ፓርቲው አሁንም አባላቱና መላው ህዝቡ በማሳተፍ እንሻገራቸዋለን ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙ አባላት በሰጡት አስተያየት ብልፅግና አካታች፣በአጭር ጊዜ በርካታ አስደማሚ ለውጥ ያስመዘገበና ሀገር ከመበተን ያዳነ ፓርቲ እንደሆነ ተናግረዋል።

አባላቱ አክለውም የተገኙ ውጤቶችና ድሎች በማስጠበቅ አሁንም ለፓርቲው ፈተና የሆኑ የዜጎች ደህንነትና ሰላም ችግር፣ የኑሮ ወረድነት፣በየአካባቢው የሚነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎች፣ጠንካራ አባልና አመራር የመፍጠርና ሌሎችም የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች በጉባኤው በተገቢ መክሮ መፍትሄ ሊቀመጥላቸው ይገባል ብለው ለዚህም የበኩላቸው እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በኮንፈረንሱ ፓርቲው በ3 አመት ውስጥ የሰራቸው ዋና ዋና ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ሪፖርት፣የፓርቲው ህገ ደንብ እና ሌሎችም ሰነዶች ቀርበው ውይይት የተደረገ በቀጣይ በፓርቲው ጉባኤ የሚሳተፉ አካላት ተመርጠዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *