የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የጥምቀት በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አስተላለፉ።

ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው የጥምቀት በዓል በሀገራችን በድምቀት ከሚከበሩ ሐይማኖታዊ በዓላት አንዱ ሲሆን በጉራጌ ዞን በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ በአደባባይ በድምቀት ይከበራል።

የጥምቀት በዓል የፍቅር፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብና የበጎነት መገለጫ በዓል ነው፡፡ ስለዚህ በዓሉ ስናከብር ጥላቻን፣ መለያየትን፣ ዘረኝነትና ቂም በቀልን በይቅርታ፣ በአብሮነትና በፍቅር በመተካት ሰላምና ደስታ የሚንሰራፋበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የዘንድሮ በዓል የህዝባችን የዘመናት ጥያቄ የነበረው የወደብ በር ጉዳይ ምላሽ እንዲያገኝ ከሶማሌ ላንድ ጋር በፈጸመችው የውል ስምምነት መሰረት የወደብ ባለቤት በሆነችበት ወቅት መከበሩ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የጥምቀት በዓል በተባሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ የባህል ተቋም (UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርስነት ከተመዘገቡ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን ቅርስ በመጠበቅና ለዓለም ይበልጥ በማስተዋወቅ ተመራጭ የቱሪስት መስህብ በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘው ሀብት ለማሳደግ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አቶ ላጫ ተናግረዋል፡፡

ጥምቀት የትህትና፣ የፍቅርና የአንድነት ምልክት በመሆኑ የኢትዮጵያውያን ለረጅም ዓመታት ጠብቀው ያቆዩዋቸውን የመከባበርና የአብሮነት እሴቶች በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመሆኑም የጥምቀት በዓልስናከብር ከሀይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር ባህላዊና ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክሩ መስተጋብሮች ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነት፣ ቋንቋ፣ ዘር፣ ባህልና የአኗኗር ዜይቤ ያላቸው ብሔር ብሐየረሰቦችና ህዝቦች በመከባበርና በመቻቻል በአንድነት በመኖር ረጅም ዘመናት ያስቆጠረች ሀገር ናት፡፡ ይህንን የቆየ እሴቶቿን ተንከባክቦ ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ ሀላፊነት የሁላችንም ይሆናል፡፡

በዓሉ ሲከበር መላው የዞናችን ህዝቦች በተለይም ወጣቶች የእምነት ልዩነት ሳይኖራችሁ በጋራ አካባቢያችሁን በማጽዳት፣ የአካባቢያችሁን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ እንዲሁም በዓሉ ለማወክ የተለየ እንቅስቃሴ የሚያደርግ አካል በሚያጋጥማችሁ ጊዜ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም በዓሉ ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይገባል፡፡ ይህንን ማድረግ በምድር በረከት በሰማይ ጽድቅ የሚያስገኝ በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች በታላቅ ትህትና ሊፈጽሙት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን አደራ በማለት በድጋሚ መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

One Comment:

  1. Today, I went to the beachfront with my children. I found a sea shell and
    gave it to my 4 year old daughter and said “You can hear the ocean if you put this to your ear.” She
    put the shell to her ear and screamed. There
    was a hermit crab inside and it pinched her ear. She never
    wants to go back! LoL I know this is entirely off topic
    but I had to tell someone!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *