የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ታላቁ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

ዋና አስተዳዳሪው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች እንኳን ለ1444ኛው ታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳቹህ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የረመዳን ወር ከፍቅር፣ ሰላም፣ መቻቻል እና መረዳዳት ጋር ልዩ ቁርኝት እንዳለው ገልፀው ይህ መንፈሳዊ ትሩፋትም ለመላው ዞናችን ብሎም ሀገራችን ሰላምና በረከት እንዲያመጣም ምኞታቸውን አክለዋል።

ሁልጊዜም ህዝበ ሙስሊም በእምነቱ አስተምህሮ መሰረት እንደሚከውነው ለሀገራችን ሰላም ፣ልማት እና ብልፅግናም አበክሮ ዱዐ እንዲያደርግ /እንዲፀልይ ጥሪያቸውን አቅረበዋል።

እንደ አቶ ላጫ ገለፃም ወሩ የሰላም እና መረዳዳት ወር በመሆኑ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ዞኑንም በሰላም እና ልማቱ የተሻለ እንዲሆን ህዝበ ሙስሊሙ እንደሁልጊዜው የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አቅርበዋል።

በድጋሚ ሰላም ፍቅር መደረዳዳትና መቻቻል ይበልጥ የሚጎለብት ወርሀ ረመዳን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *