የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አሰርቶ ያጸደቃቸው የከተሞች ፕላን ለወረዳዎች አስረከበ።

ነሀሴ 28/2014 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አሰርቶ ያጸደቃቸው የከተሞች ፕላን ለወረዳዎች አስረከበ።

ከተሞች እድገታቸው ለማፋጠንና ለኑሮ አመቺ ለማድረግ በፕላን ሊመሩ እንደሚገባ መምሪያው አስታውቋል።

የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትልና የከተሞች ፕላን ኢኒስቲቲዩት ኃላፊ ወ/ሮ ሸሚማት ለሻድ እንደተናገሩት ከተሞች እድገታቸው ለማፋጠንና ለኑሮ አመቺ ለማድረግ በፕላን ሊመሩ ይገባል።

ይህንን ፕላን ለማሰራት መጀመርያ ሲኤች ፕላን መሰራቱና ከዚያ በኋላ 8 መሰረታዊ ፕላኖችን ማሰራት መቻሉ የተናገሩት ኃላፊዋ በፕላን ዝግጅቱ ጂኦግራፈሮች፣የሶሽዮ ኢኮኖሚ፣የሰርቨሪንግ፣የፕላን ባለሙያዎችና የማኔጅመንት አካላት ተሳትፈውበታል ብለዋል።

ወ/ሮ ሸሚማት አክለውም የዚህ ፕላን ማሰራት ከተሞች ወደ ከተማ አስተዳደርነት ለማሳደግ፣የከተሜነት መስፈርት በማሟላት እንደ ሀገር አቀፍ ታውቀዉ እውቅና እንዲሰጣቸው ለማድረግ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በዞኑ ከ4መቶ ቀበሌዎች ውስጥ 48ቱ ከተሞች እውቅና ያላቸው ሲሆኑ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ከተሞች እውቅና የሚያገኙ ናቸው ብለዋል።

ሰዎች በአሉበት አካባቢ ጸንተው እንዲኖሩ፣የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ፣አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ለገበያ ለማቅረብ፣ህገ ወጥ የመሬት ወረራና የቤት ግንታ ለመቆጣጠር፣ከተሞቹ ከብልሹ አሰራር ለማውጣት እና ለሌሎች ተግባራት የከተማ ፕላን ወሳኝነት አለው ነው ያሉት።

ይህ የከተማ ፕላን ለ10 አመት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አንድን ከተማ በ10 አመት ውስጥ ምን እንደሚያስፈልገውና ምን መሆን እንደሚችል አስፍቶ እንዲያሳይ መሰራቱ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

በተለይም በትምህርት፣በጤና፣በመዝናኛ ቦታ፣በስነ ህዝብ ብዛት፣በአጠቃላይ በከተማው ምን እንደተሰራና ቀጣይ ምን እንደሚሰራ የሚያሳይ መሆኑን አብራርቷል።

ከተሞቹ ለማሳደግ እንዲሁም ፕላናቸው ለመስራት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉንና 4መቶ ሰዎች ተስማምተው መፈረማቸው የገለጹት ወ/ሮ ሸሚማት ከተሞች በተሰራላቸው ፕላን መሰረት እንዲለሙ ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ቀጣይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በወረዳ ምክር ቤቶች አጽድቆ በፕላኑ መሰረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ወ/ሮ ሸሚማት።

ያለ ፕላን የሚሰሩ ቤቶች መፍረሳቸው ስለማይቀር እነዚህ ግንባታዎች ከፈረሱ ደግሞ በሀገር ኢኮኖሚ ጫና የሚያሳድሩ በመሆናቸው ያለ ፕላን ማንኛውም ግንባታ መሰራት እንደሌለበት ገልጸዋል።

የመምሪያው የከተሞች ፕላን ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አብራር ለጂብ እንዳሉት ፕላኖቹን ለማሰራት ከፍተኛ የሆነ በጀት ቢፈልግም ይህን ለመቀነስ በተከሄደው እርቀት ግን በትንሽ ወጪ በርካታ ስራ መሰራቱ ተናግረዋል።

10 ፕላኖች ለማሰራት ታቅዶ 8ቱ የተከናወነ ሲሆን በማረቆ፣ሶዶ፣ እኖር ኤነር መገር፣አበሽጌ፣ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳዎች ላይ ሲሆን ቀሪ 2ቱ በቸሀና በእዣ ወረዳ ለመስራት በሂደት ላይ ይገኛሉ ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *