የጉራጌ ዞን አስተዳደር የአረፋ በዓል በመቄዶንያ አረጋውያንና አይምሮ ህሙማን ጋር ማክበሩ ለአቅመ ደካማ አረጋውያንና ለአእምሮ ህሙማን ያለው ትልቅ ክብር ማሳያ መሆኑን የማእከሉ መስራችና ባለቤት ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ተናገሩ።

ይህ የተናገሩት የጉራጌ ዞን አስተዳደር የአረፋ በዓል በመቄዶንያ ከአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን ጋር በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት ነው።

የመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራችና ባለቤት ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ እንዳሉት የዞኑ አስተዳደር የአረፋ በዓል በማዕከሉ በመገኘት ለማክበር ያደረጉት በጎ ተግባር ለአረጋውያንና ለሀገር ያላቸው ትልቅ ክብር ማሳያ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በዓሉ ከ4 ሺህ አሪጋውያንና አዕምሮ ህሙማን ማዕድ በማጋራት ከማክበራቸውም በተጨማሪ ለተቋሙ 5 መቶ ሺ ብር እና የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ፣ የብርደልብስ፣ የአንሶላና የፍራሾችና ድጋፍ ማድረጋቸው ለእርዳታና ለበጎነት ከፍተኛ ቦታ እንዳላቸው ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ለማእከሉ ለተደረገው ድጋፍ በማመስገን በቀጣይ ይህ በጎ ተግባርም ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል

የመቄዶንያ ማዕከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ እንደሚገኝ ገልፀው አሁን ማዕከሉም ከ7 ሺ በላይ አቅመ ደካማ አረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን እየረዳ ይገኛል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር በወልቂጤ ከተማ ለመቄዶንያ 10 ሺ ካሬ መሬት እንደሰጣቸው አስታውሰው ከስራው ስፋት አንፃር ተጨማሪ መስሪያ ቦታና በአረጋውያን የተመረቱ ምርቶች መሸጫ የንግድ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በቀጣይ በቡታጅራም ማዕከሉ ለማቋቋም እቅድ እንዳላቸው ገልፀው ለንግድ፣ ለማእከሉ የሚሆን ቦታ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ገብረመድህን በማህበረሰቡ ዘንድ የአረፋ በዓል የመረዳዳትና የመተሳሰብ በዓል በመሆኑ ይህንን መሰረት በማድረግ የአረፋ በዓል መቄዶንያ ከሚገኙ አቅመ ደካሞች ጋር በጋራ ለማክበር ያለመ እንደሆነ ጠቁመው በቀጣይም የማህበረሰቡን እሴት ለማስቀጠል ባህላዊና ሀይማኖታዊ ይዘቱን ሳይለቅ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በምገባና ድጋፍ ፕሮግራሙ የተገኘው የካሊድ ፋውንዴሽን አስተባባሪ ወንድም ካሊድ ናስር ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስርቶ ከሀገራችን በ4ቱም አቅጣጫ ግንባታሀይማኖት፣ ብሔር፣ ፆታና ሌሎች ልዩነቶች ሳይፍጥር ለአቅመ ደካማ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን በአንድ አሰባስቦ ሁሉ አቀፍ እገዛ በማድረጉ ሊመሰገንና ሁሉም የበኩሉን እገዛ ሊያደርግለት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የጉራጌ ማህበረሰብ ስራ ወዳድና ሰው አክባሪ እንዲሁም የተቸገረ የመርዳት የቆየ ባህል በመጠቀም የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አረጋውያንን፣አዕምሮ ህሙማንና ሌሎችም የሚቸገሩ ወገኖች መርዳትና መልሶ ማቋቋም እንዲቻሉ ሁሉም ተቀናጅቶ መስራት አለበት እርሳቸውብለዋል።

አርቲስት መሀመድ ሚፍታ በዓሉ ባከበሩበት ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያውያን ተካፍሎ መብላት ባህላችን በመሆኑ በወቅቱ ከተፈጠሩ ጊዜያዊ ችግሮች አንፃር መተጋገዝ እንደሚገባ ጠቁመው በዓሉ በሚከበርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በማካፈል ሊሆን ይገባል ብለዋል።

መቄዶንያ ለሚገኙ ተረጂ ወገኖች የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ማዕድ ማጋራቱና የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተካፍሎ የመብላት ባህላችን የሚያሳይ ነው ያሉት ።

አክለውም አርቲስት መሀመድ ሚፍታ የመረዳዳት የመደጋገፍና የመተሳሰብ አኩሪ እሴታችን አጠናክሮ በማስቀጠል በሁሉም አከባቢ ላሉ አቅመ ደካሞችና አእምሮ ህሙማን መርዳት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ባላቸው ሙያ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የበኩላቸውን እገዛ እያደረጉ መሆኑን ተናግረው መላው የሀገራችን ህዝብ በማዕከሉ ለተሰባሰቡ ወገኖች በአይነት፣ በገንዘብ አንዲሁም በ8161 A ብለው በመላክ የበኩላቸውን እንዲወጡ ሲሉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *