የጉራጌ ዞን አስተዳደር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመንግስት ሰራተኞች የከፍተኛ የትምህርት እድል በማመቻቸት እድል ተጠቅመው የሁለተኛ ዲግር ትምህርት በማጠናቀቃቸዉ ደስተኛ መሆናቸዉ አንዳንድ ተመራቂዎች አስታወቁ።

ሀገር እንድትለወጥ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከታለመ መንግስት እንደዚህ አይነት የትምህርት እድሎች ለመንግስት ሰራተኞች ማመቻቸቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተመራቂዎቹ ተጠቁሟል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና የጉራጌ ዞን አስተዳደር በጋራ በመሆን በተመቻቸላቸዉ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ከሆኑት አቶ አብዶ ሀሰን ፣ አቶ መሀመድ ጀማል ፣ ወይዘሮ አሰለፈች ገብረስላሴ ፣ አቶ አብድላዚዝ በረዳና አቶ እንዳለሽብሩ አበራ  የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ተከታትለዉ ከተመረቁ የመንግስት ሰራተኞች መካከል ይጠቀሳሉ።
አቶ አብዶ ሀሰን በኢኮኖሚክስ የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ሲሆን በ2012 አመተ ምህረት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና የጉራጌ ዞን አስተዳደር  በወረዳና በዞን ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ  ባመቻቸዉ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ በመሆኔና በመመረቄ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ህብረተሰቡን ለማገልገልና ሌሎችም የስራ እድሎችን በመፍጠር ከመቼዉም ጊዜ በላይ ለመስራት ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸዉም አብራርተዋል።

አቶ መሀመድ ጀማል በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ስነ -ጹሁፍ የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆን የዞኑ አስተዳደር ሲቪል ሰርቫንቱ ከለዉጡ በኃላ በትምህርት እንዲጎለብት ለማድረግና ሰራተኛዉ ዉጤታማ ስራ እንዲሰራ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በዞኑ በተለያዩ ተቋማት የሚያገለግሉ ሰራተኞችን የትምህርት ደረጃቸዉን እንዲያሻሽሉ እድል ፈጥሯል ብለዉ የሁለተኛ ዲግሪዉ ሳስበዉና ሳልመዉ የነበረዉን የህልሜን የመጀመሪያዉን ምዕራፍ  ዩኒቨርሲቲዉና አስተዳደር ባመቻቹት እድል ማሳካት ችያለሁኝ ብሏል።
አንድ ሀገር ሊለዉጥ የሚችለዉ ትምህርት ነዉ ያሉት አቶ መሀመድ ሰዎች በእዉቀት ከፍ ባሉ ቁጥር ማህበረሰብን የማገልገል ዕድላቸዉ ይሰፋል ብለዉ የሰራተኞች ሙያዊ ስነ ምግባራቸዉ የማክበር ሁኔታ ከእዉቀት ጋር የታገዘ እንደሆነም ጠቁመዉ ሀገር እንድትለወጥ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከታለመ መንግስት እንደዚህ አይነት ለመንግስት ሰራተኞች ዕድሎች ማመቻቸት እንዳለበትም አብራርተዋል።
ሌላኛዉ እድሉን አግኝቶ በሁለተኛ ዲግሪ በማኔጅመንት የተመረቀዉ አቶ እንዳለሽብሩ አበራ እንዳሉት በተመቻቸላቸዉ እድል በመመረቃቸዉ ጀስተኛ እንደሆኑም ተናግሯል። በተመረቁበት የሙያ ዘርፍ ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት  ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸዉም ተናግረዋል።

ወይዘሮ አሰለፈች ገብረስላሴ በወልቂጤ ዪኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ተከታትላ ተመርቀዋል። ዞኑ ይህንን እድል ያመቻቸዉ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተናግረዉ በዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናቸው በጣም ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
መንግስት በስራቸዉ ግንባር ቀደም ሰራተኞችን መርጦ ለማበረታታት ያመቻቸዉን ዕድል አርአያ ሊሆን የሚችል እንደሆነም አብራርተዉ ይህንንም ዕድል ለስራቸው ተነሳሽነት ያላቸዉን ሌሎች ባለሙያተኞች በቀጣይም እንዲያገኙ በማድረግ የተሻለ ዉጤታማ ስራ ይሰራል ብለዋል።
የሁለተኛ ዲግሪ የአካዉንቲንግና ፈይናንስ ተመራቂ ተማሪ አቶ አብድላዚዝ በረዳ የጉራጌ ዞን አስተዳደር የመንግስት ሰራተኛዉ የማስተርስ ትምህርት እድል በማመቻቸቱ ደስተኛ መሆናቸዉም ተናግረዋል።
በዩኒቨርስቲ ቆይታቸዉ ያገኙትን እዉቀትና ክህሎት በመጠቀም በሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሚያስችላቸዉም አስረድተዋል።
ሌሎችም ሰራተኞች የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት እድል ከተመቻቸላቸው በየተቋማቶች የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያስችላቸዉም አስታዉቀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የጀመረዉን በጎ ተግባር ቀጣይነት ሊኖረዉ እንደሚገባም አብራርተዋል።
በየተቋማቶቹ በአፈጻጸም የተሻሉ ሰራተኞችን የመማሩ እድል በማመቻቸት ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸዉም ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *