የጉራጌ ዞን አስተዳደር አጠቃላይ ስራዎች ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ተቀራርበዉ እንደሚሰሩ የአይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ ወጣት ኢዘዲን ካሚል አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊና አጠቃላይ ባለሙያተኞች የአይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ካምፓኒና የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስትቲዩት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንዳሉት ተቋሙ ዉጤታማ እንዲሆን ከስራዉ ጋር ግንኙነት ያላቸዉ ጠቃሚ የሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት ልምድ በመዉሰድና በጋራ በመስራት የተሻለ ዉጤት እንዲመጣ አበክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የመምሪያዉ አጠቃላይ ባለሙያተኞች በቀጣይ አመት የተሻለ ስራ ለመስራት ጥሩ ልምድ እንዲወስዱ በየአመቱ ከስራቸዉ ጋር የሚገናኙ የተለያዩ ተቋማቶች ጉብኝት ይደረጋል ብለዉ በትላንትናዉ ዕለት የአይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ካምፓኒና የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስትቲዩት በጋራ መስራት የሚያስች ጉብኝት እንዳደረጉም ተናግረዋል።

ኢዘዲን ካሚል የሚመራዉ አይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ካምፓኒ በዞኑ ብዙ ሊሰራቸዉ የሚገቡ ተግባራቶች መኖራቸዉም አንስተዉ እንደ ሀገር የተያዘዉን 2025 ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመፍጠርና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙ ብዙ ቴክኖሎጂዎች ፣ ዌብሳይቶችን ፣የሞባይል መተግበሪያ አፕልኬሽኖች የፈጠረዉ አይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን በጋራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ዞኑ ቀድሞ ዲጂታላይዝድ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዉ ለሀገር ትልቅ ጥቅም የሚሰጡ ከጉራጌ ዞን የወጣዉ የብዙ የፈጠራ ስራዎች ባለቤት ድርጅት በመጎብኘታቸዉና ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸዉም አመላክተዋል።

ተቋማቸዉ በ2017 ከወረቀት ነጻ የሆነ ዲጂታላይዝ አሰራር ለመዘርጋት አቅደዉ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም አመላክተዉ ለዚህም ስኬት የአይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ ኢዘዲን ካሚል ጋር በጋራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ካምፓኒዉ የሚሰራቸዉ አጠቃላይ ስራዎች የመምሪያዉ አጠቃላይ ሰራተኞች ማየታቸዉ በቀጣይ በዘርፉ የተሻለ ስራ መስራት የሚያስችላቸዉም እንደሆነም ጠቁመዋ።

ካምፓኒው የበለጠ ማስተዋወቅ እንደሚገባና ወጣቱም በዞኑ በፈጠራ ስራ ለተሰማሩ ተማሪዎችና ወጣቶች ያነቃቃና ለበዙዎች ተምሳሌት የሚሆን እንደሆነም ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ተቋም እንደ ሀገር ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዉ ኢንስቲዉቱም በተለይ በዞኑ በቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራ ላይ ያሉ ልጆችን በተገቢዉ በማወዳደር ወደዚህ ተቋሚ የሚገቡበትን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠርም አስታዉቀዋል።

በፈጠራ ስራ የተሰማሩ ልጆች በማወዳደርና የሰራቸዉ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተግባር ቀይረዉ ለታለመለት አላማ እንዲዉል ለማስቻል የሚችሉበት ተቋም መሆኑም ያዩበት ተቋም እንደሆነም ያብራሩት አቶ ደምስ ተቋሙ በስልጠና ፣ በማቴሪያል ድጋፍና በፈጠራ ስራ የተሰማሩ ተማሪዎች እዚሁ አምርተዉ ወደ ገበያ ለሚያወጡበት የሚችሉበት ሰነድ በአጭር ጊዜ ዉስጥ የግብ ስምምነት እንደሚፈራረሙም ጠቁመዋል።

የአይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ወጣት ኢዘዲን ካሚል እንደሚለዉ ድርጅቱ ሶፍትዌር ማበልጸግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይሁን ዞኑ ከካንፓኒዉ ጋር በቅርበት ቢሰራ የበለጠ ዉጤታማና አሰራሩን ዲጂታላይዝድ ማድረግ ያስችለዋል ብለዉ

ድርጅታቸዉ ከሀገር ዉስጥና ከተለያዩ የአለም ሀገራት ትላልቅ ድርጅቶች ተቀበለዋቸዉ እየሰሩ እንደሆነና ከሰባት በላይ ለሚሆኑ ለዉጭ ሀገራት የሞባይል አፕልኬሽኖች ፣ኢንተርናል ሲስተሞችና ሶፍትዌሮች የማበልጸግ ስራም መስራታቸዉም አብራርተዋል።

ድርጅቱ እስከ 2025 ስራዎች በሙሉ ዲጂታላይዝድ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዉ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ፍቃደኝነቱን ስላሳየን ለሀገሪቷ ተምሳሌት የሚሆኑ አጠቃላይ ስራዎቹ ዲጂታላይዝድ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።

ዞኑ በቴክኖሎጂ እንደ ሀገር ተምሳሌት እንዲሆን ተቀራርበን እንሰራለን ብለዉ የጉራጌ ዞን አስተዳደርም የአይካርድ ተጠቃሚ በማድረግ ስራዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ማከናወን እንዳለበትም ተናግረዋል።

ኢንኩቤሽን ማዕከል ቢመቻች ወጣቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራዉ ዘርፍ የሚፈለገዉ ወጤት እንዲመጣ ከዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተናግሯል።

በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የኢንደስትሪ ትስስር ዳይሮክቶሬት ዶክተር የማነህ ዘሚካኤል እንዳሉት የሰመር ካም ሰልጣኞች በኢትዮጵያ ደረጃ ዉድድር የሚካሄድና ትልቅ ራዕይ ያለዉ ፕሮግራም እንደሆነም ተናግረዉ ይህም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲሁም ከኢንተርፕረነር ሺፕ ኢንስትትዩት በጋራ የሚሰራ ስራ ሲሆን ለዚህም ተገቢዉን በጀት ተመድቦለት እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

በቅርቡ ማንኛዉም የፈጠራ ስራ ያላቸዉ ሰዎች ተወዳድረዉ ወደ ተቋሙ የሚገቡና የፈጠራ ስራዎቻቸዉ አበልጽገዉ ለገበያ እንዲያቀርቡ ይደረጋል ብለዋል።

ተቋሙ በቀጣይ መምሪያዉ ለሚጠይቀዉ የስልጠናና መሰል ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑም አመላክተዋል።

በጉብኙቱ የተገኙ አንዳንድ የመምሪያዉ ባለሙያተኞች በሰጡት አስተያየት በዞኑ በርካታ የፈጠራ ስራ የሚሰሩ ታዳጊዎች መኖራቸዉም አስታዉሰዉ እነዚህም በተለያዩ ስልጠናዎች እንዲታገዙና በዘርፉ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ቴክኖሎጂዎች መፍጠር እንዲችሉ አይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ካምፓኒ እንዲሁም በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዉት የተከፈተዉ ስቲም ፓወር አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የአይቤክስ ቴክኖሎጂና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ለወጣት ኢዘዲን ካሚል መምሪያዉ የእዉቅና ሰርተፍኬት ያበረከተለት ሲሆን እንዲሁም በመምሪያዉ በበጀት አመቱ የተሻለ ስራ የሰሩ ባለሙያተኞች የእዉቅናና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *