የጉራጌ ዞን አስተዳደር በቀቤና ወረዳ በሌንጫ ቀበሌ በእሳት አደጋ ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው አባወራዎች 1ሺህ 2 መቶ የቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ አደረገ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጸህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፍ አካሉ ድጋፉ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት የደረሰው ጉዳት እጅግ አሳዛኝ ከመሆኑም ባሻገር በአደጋው ምክንያት ለብዙ አመታት ለፍተው ያፈሩት ቤትና ንብረት እንዲሁም በዙሪያው የሚገኙ ሰብሎችም ጭምር ወድመዋል ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ተጎጂ ቤተሰቦችን ፈጥኖ በማደራጀት ወደ ነበሩበት ህይወት እንዱመለሱ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል ።

ተጎጂዎችም በወገንና በመንግስት ድጋፍ በአጭር ጊዜ ወደ ቀድሞው ኑሯቸው ይመለሳሉ ብለዋል።

የዞኑ መንግስት ከ720 ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው አንድ ሺ ሁለት መቶ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ለተጎጂዎች ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል።

አቶ አሰፋ አክለውም ተጎጀዎችን በዘላቂነት ለማደራጀትና ወደ ነበሩበት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ሁለንተናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የቀቤና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የተጎጂዎች ሃብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብድርሽኩር ደሊል ድጋፉ በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት አደጋው ከተከሰተ ማግስት ጀምሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር በተለያየ መልኩ ለተጓጂዎች ፈጥኖ በመድረስ እያደረገ ላለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል የአደጋው ተጎጂዎች በጎበኙበት ወቅት እነዚህ ቤተሰቦችን ፈጥኖ ለማደራጀትና ወደ ነበሩበት ለመመለስ የዞኑ መንግስት የቆርቆሮ ድጋፍ ባጭር ጊዜ እንደሚያደርግላቸው በገቡት ቃል መሰረት ዛሬ በተደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል ።

ኮሚቴው እስካሁን የምግብ ፣የአልባሳት፣ የቤት መስሪያ የሚወሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን በማስተበሰበር ሃብት በማሰባሰብ ላይ እንደነበረ ገልፀው በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ግንባታ ስራ በመግባት ባጭር ጊዜ አጠናቆ ለተጎጂዎች ለማስረከብ ሰፊ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

ከዚሁ ጎንለጎን ወቅቱ የበልግ አዝመራ ሰዓት በመሆኑ በአደጋው የተቃጠሉ እህሎችን ለማካካስ በሚያስችል መልኩ የአካባቢው ማህበረሰብ በስተባበር ማረስ እንዳለባቸው ገልፀው የምረጥ ዘር አቅርቦት በወረዳው መንግስት በኩል ይሸፍናል ብለዋል።

ተጎጂዎችም የጉራጌ ዞን አስተዳደር ላደረገላቸው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅረበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *