የጉራጌ ዞን አስተዳደር ለወንድም የኦሮሞ ህዝብ እንኳን ለኢሬቻ የምስጋና በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ፡፡

ኢሬቻ የምስጋና በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ምድር እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪው ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በኢሬቻ ቀን ምስጋናውን ለፈጣሪ ያቀርባል።

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ መሆኑን ዋና ጠቅሰው በዓሉ የምስጋና፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የእርቅ እና የይቅርታ ተምሳሌት፣ የተራራቀ የሚገናኝበት አኩሪና ድንቅ በዓል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በክረምት ወራት ተራርቆ ሳይገናኝ የቆየ ዘመድ አዝማድ መስከረም ላይ ይገናኛል። ሕዝቡም ክረምቱን በፈጣሪ ፍቃድ የሞላው ውሃ ጎድሎ ከዘመድ አዝማድ አገናኝን ብሎ ምስጋና ያቀርባል። ከጨለማ ወደ ብርሃን ላሸጋገረው አምላክም ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው ብለዋል።

የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ተሠብስቦ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ነው፡፡ የሰው ልጅ በማህበራዊ ደረጃው፣ በሀይማኖት፣ በዘር እና በጎሳ ሳይለይ ወንዱም ሴቱም ልጅ አዋቂ ሁሉንም የሚያሳትፍ የአንድነት፤ የህብረትና የመሰባሰብ፤ የተጣሉ የሚታረቁበት፤እንዲሁም የፍቅር ለፍጥረታት ሁሉ ርህራሬን የምናሳይበት ባህላዊ እሴት ነው፡፡

የኢሬቻ በዓል የአብሮነት፣ የአንድነት እና የእርቅ በዓል ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያ የበርካታ ድንቃድንቅ ተፈጥሮ ፤ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት ባለቤት ነን፤ በርካቶች ያልታደሉትን ፀጋ እኛ ተችረናል፡፡ በቁጥር ተዘርዝረው የማያልቁ የየራሳቸው ቀለማት ያሏቸውን ህዝባዊ በዓላት በጋራ እናከብራለን፡፡

በብዝሃነታችን ውስጥ የሚታዩት ህብረ ቀለማት የውበታችን ምንጭ እና የአንድነታችን መሰረቶች ስለሆኑ በጋራ ልንጠብቃቸው በጥሩ መሰረት ላይ አኑረን ከትውልድ ትውልድ ልናሸጋግራቸው ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መልካም የኢሬቻ በዓል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *