የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2015 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈጸጸም በወልቂጤ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።

በግምገማ መድረኩ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም የመምሪያው የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።

በትምህርት ዘመኑ የመምሪያውና የተመረጡ (የቸሃ፣ የምስራቅ መስቃን፣ የሶዶ እና የእንደጋኝ) ወረዳዎች የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም እና የመመሪያው የአንደኛ ዙር መደበኛ ሱፐርቪዥን ግብረመልስ ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል።

የግምገማው ዝርዝር መረጃ አጠናቅረን እናቀርባለን። የእኛን የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመረጃ ምንጭነት ስለሚጠቀሙ እናመሰግናለን !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *