የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያና በስሩ የሚገኙ 11 የመንግስት ኮሌጆች ለመከላከያ ሰራዊት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንቅ ድጋፍ አደረጉ።

በዞኑ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና መምሪያው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሙሉ በሙሉ እኪደመሰስ ድረስ ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ ወ/ሮ ማርታ ሎዊጂ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት የኢትዮጵያ ህዝቦች በአንድነት ሆነው ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ ጁንታው በመደምሰስ ከፍተኛ ድል ተገኝቶዋል።

ህዝቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ ለሠራዊቱ የሞራል ስንቅ ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ ማርታ እስካሁን ለተደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ጦሩ ከፍተኛ ምስጋና አለው ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈቱ አብዶ ድጋፉን ለመከላከያ ሰራዊት ሲያስረክቡ እንደገለጹት የመከላከያ ሰራዊት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ደጀን ለመሆን የዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያና በስሩ የሚከገኙ 11 የመንግስት ኮሌጆች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የስንቅ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።

የጉራጌ ዞን ማህበረሰብ በሀገሪቱ የህልውና ዘመቻ ከተጀመረ ጀምሮ ከ148 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና ጥሬ ብር ለመከላከያ ሰራዊትና በጦርነቱ ሳቢያ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

በቀጣይም ጁንታው ሙሉ ለሙሉ ተደምስሶ ሀገሪቱ ወደ ልማት እስክትመለስ ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገውን ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ፈቱ አብዶ ተናግረዋል።

የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲንና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሄይሩ አህመዲን በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው የተቃጣባቸውን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ ለመመከት ባደረጉት ብርቱ ጥረት አሸባሪው እየደመሰሱ ወደ ናፈቀው ሲኦል እየሸኙት ይገኛል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያና በስሩ የሚገኙ 11 የመንግስት ኮሌጆች ከዚህ ቀደምም ለመከላከያ ሰራዊት ደም መለገስ፣ የዘማች ቤተሰብ ሰብል መሰብሰብና መንከባከብ እንዲሁም ለህዝባዊ ሰራዊት የደንብ ልብስ ድጋፍ አድርገዋል ያሉት አቶ ሄይሩ አህመዲን በቀጣይም ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ ጠላቶች የተቃጡባትን ወረራ ሙሉ ለሙሉ እስክትቀለብስ ድረስ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

=አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *