የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል ለመላው የዞናችን ማህበረሰብ ብሎም ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል ለመላው የዞናችን ማህበረሰብ ብሎም ኢትዮጵያውያን ለአዲሱ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዲሱ አመት የሰላም የጤና እና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አዲሱ ዓመት ለዞናችን ማህበረሰብ ብሎም ለክልላችን ልዩ ትርጉም አለው ያሉት አቶ አለማየሁ በአዲስ ምዕራፍ የጀመርናቸው ቁልፍ የልማት ስራዎች ከዳር በማድረስ ፣ በአብሮነት የበለፀገ አመት እንዲሆን ልባዊ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በ2016 እንደ ዞን የተሻሉ ማህበረሰቡን ያስጠቀሙ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀው በአዲሱ አመትም በአዲስ መንፈስ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ይሰራሉ ያሉት አቶ አለማየሁ መላው የዞኑ ማህበረሰብም እንደ ቀድሞው አንድነቱን ጠብቆ የተጀመሩ ውጥኖች ከዳር እንዲደርሱ እገዛው ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በዓሉምን ስናከብር የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴቶቻችንን አጎልብቶ ከተቸገሩ ወገኖች ጎን ሆኖ አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በድጋሚ ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ አዲሱ አመት የፍቅር የሰላም፣የመተሳሰብ እና የብልፅግና ብሩህ አመት እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

                 መልካም አዲስ አመት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *