የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽህፈት ቤት የ2016 ግማሽ አመት ተግባር አፈጻጸምና የ2ተኛ ግማሽ አመት የተከለሰ እቅድ ላይ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ጋር በወልቂጤ ከተማ ውይይት አካሂዷል።


በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቅባቱ ተሰማ እንዳሉት የመድረኩ አላማ በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች በተግባር አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ልዩነቶችን ለማጥበብና ወጥ በሆነ መልኩ እንዲፈጸሙ ለማስቻል ነው።

ከአባላትና ከአመራር የሚሰበሰበው መዋጮ በአግባቡ እየተሰበሰበ እንደሆነ ጠቁመው ይህም በተገቢው ወደ ክልሉ መላክ እንዳለበት ተናግረዋል።

እንደ አቶ ቅባቱ ገለጻ ከወረዳ ጀምሮ እስከ መሰረታዊ ፓርቲ ድረስ የኮሚሽን ኮሚቴ የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል።

በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ጽህፈት ቤቶችን ግብአት ከሟሟላት አንጻር በአብዛኛው የተሻለ ቢሆንም አሁንም የሚቀሩ ስራዎች ከፓርቲ አመራሮች ጋር ማስተካከል ይገባል ብለዋል።

የኮሚሽን አመራሩ መመሪያና ደንቡ በመረዳትና በመገንዘብ ፓርቲው የመሰረተው መንግስት ላይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ቀድሞ ለመከላከል የዘርፉ አመራሮች በየደረጃው ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

ፓርቲው የያዛቸው ግቦችና አላማዎችን እንዲሳኩ ዘርፉ ሚናው የላቀ መሆኑን ያነሱት አቶ ቅባቱ ፓርቲው የሚያጋጥሙት ፈተናዎችን በብቃት በማለፍ የህብረተሰቡን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንዲቻል የዘርፉ አመራሮች በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የዘርፉ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከፓርቲ ጽህፈት ቤት በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት ዞኑ በዚህ ልክ መድረክ ፈጥሮ ውይይት መደረጉ በዘርፉ ያሉ ስራዎችን በአግባቡ ወስዶ ለመስራት ያግዛል ብለዋል።

መመሪያዎችና ደንቦችን በአግባቡ በመገንዘብ ስራዎችን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አንስተው ለዚህም የአቅም ማጎልበት ስልጠና እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

ከዚህም ባለፈ ተግባራት በወቅቱና በተገቢው ለመፈጸም የግብአት እጥረት ተግዳርት እንደሆነባቸው አንስተው እነዚህም ተግዳሮቶች ሊፈቱ እንደሚገባም አንስተዋል።

በተግባር አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ ስራዎችን በማስቀጠልና በግማሽ አመቱ ያልተከናወኑ ተግባራት በቀጣይ በትኩረት አቅደው እንደሚሰሩ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *