የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ማኔጅመንት አካላት ባለሙያዎችና የምክር ቤት የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎች በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የቆጠር ገድራ ኪዳነ ምህረት ገዳምና መስህቦች ጎበኙ።

በዞኑ የሚገኙ ታሪካዊና ጥንታዊ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቁ ስራ ላይ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው መምሪያው አስታውቀዋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ገብረመድህን የጉብኝቱ አላማ የሀገርህን እወቅ ክበባትን ለማነሳሳትና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን በማበረታታት የቱሪስት መስህቦችን እንዲጎበኙና እንዲተዋወቁ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ ተመስገን ገለጻ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ያሉ የሀገርህን እወቅ ክበባት በማጠናከር የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በባለድርሻ አካላት የተጎበኘው ጥንታዊና ታሪካዊው የቆጠር ገድራ ኪዳነ ምህረት ገዳምና የተፈጥሮ ደን፣ ዋሻዎችና ቅርሶች ህብረተሰቡ እንዲጎብኛቸው ከማድረግ ባሻገር ሌላው ማህበረሰብ እንዲያውቃቸው ለማድረግ ነው ብለዋል።

በዞኑ የሚገኙ ጥንታዊ፣ ታሪካዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ይዘታቸውን ሳይለቁ በማቆየት ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ እንደሚሰራም ኃላፊው ተናግረዋል።

በዞኑ የሚገኙ የቱሪዝም ቦታዎችን በመለየት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በቀጣይም በማስተዋወቁ ስራ ላይ ባለሀብቶች፣ ሚዲያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ ጠጄ ደነቀ በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ የሚገኘው ታሪካዊና ጥንታዊ የቆጠር ገድራ ኪዳነ ምህረት ገዳምና የተፈጥሮ ደን እንዲጎበኙና እንዲተዋወቁ የተጀመረው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው ይህ ተግባርም በሌሎችም መዋቅሮች በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በቀጣይ በዞኑ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን በማልማቱና በማስተዋወቁ ስራ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የቆጠር ገድራ ኪዳነ ምህረት ገዳም መምህር አባ ኤልሳ ናርዶስ እንዳሉት በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ የተፈጥሮ ደኖችን፣ ቅርሶችንና ዋሻዎችን በመጠበቅ፣በመንከባከብ ወደ ገዳሙ ለሚመጡ ጎብኚዎች እያስጎበኙ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በተለይም በሀገሪቷ እየተመናመነ የመጣው ደንና ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ያሉት አባ ኤልሳ መምሪያው ገዳሙ፣የተፈጥሮ ደኑና ሌሎችም ቅርሶች እንዲጎበኙ እንዲተዋወቁ ያደረገው ተግባር አመስግነዋል።

ገዳሙ ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው የቱሪስት ፍሰቱ የበለጠ እንዲሳለጥ የመንገድና የመብራት ችግር መኖሩና በገዳሙ የሚገኙ ዋሻዎቹና ቅርሶች ለቤተክርስቲያኒቷ እውቅና በመስጠት በጥናት ያልተረጋገጡት እንዲረጋገጡ እገዛ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አቶ አሰበ ፋንቱና ወይዘሪት ፋሲካ አስራ በጋራ በሰጡት አስተያየት መምሪያው ባመቻቸላቸው እድል ገዳሙና የተፈጥሮ ደኑ በማየታቸው በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት መነሳሳትን እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

በዞኑ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በመጠበቅ፣ በማልማትና በማስተዋወቅ እንዲሁም በአለምና በሀገር አቀፍ ደረጃ በቅርስነት እንዲመዘገቡ በማድረግ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን እንዲጎበኙት መምሪያው የጀመረው ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል። የበኩላቸዉን እንደሚወጡ በመጠቆም፡፡

በመጨረሻም ከጉብኝቱ ጎን ለጎን መምሪያው በቤተክርስቲያን ለተጠለሉ ነድያን ማእድ የማጋራና በመምሪያው ረጅም አመታት ያገለገሉ ሰራተኞችን ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *