የጉራጌ ዞን ስፖርት ልዑክ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ ክልሉ ባዘጋጀው ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ወድድሮች ላይ ተሳትፎ ከአጠቃላይ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች 3 ደረጃ በመውጣት የ15 ዋንጫዎችና የ81 የተለያዩ ሜዳሊያዎችና 15 ዋንጫዎች ተሸላሚ መሆን መቻሉን የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለጸ፡፡

በስፖርቱ ዘርፍ ዞኑን ብሎም ሀገሩን የሚያስጠሩ ጠንካራና ተፎካካሪ ስፖርተኞችን የማፍራት አቅም እንዳለው ተገልጿልም።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖረት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅማቶ እንደገለጹት በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ አስተናጋጅነት የደቡብ ክልል አጠቃላይ የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮን እና የባህል ስፖርት ፊሲቲባል ከ18-05/2014-03-06/2014 ዓ.ም ለ 15 ቀናት በተካሄደው ውድድር ከ1 መቶ 54 በላይ ዞኑን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን በመያዝ በ11 የውድድር አይነቶች ላይ በመሳተፍ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
በ2014 የጉራጌ ዞን 8 ተኛው የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮንና 19 ኛው የባህል ስፖርት ውድድር በዞን ደረጃ በቡታጅራ ከተማ ማካሄዳቸውንና በዚህም ምርጥና ተተኪ ስፖርተኞችን በመለየት ክልሉ ባዘጋጀው ውድድር በመሳተፍ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ይህም ውጤት በስፖርቱ ዘርፍ ዞኑን ብሎም ሀገራችንን የሚያስጠሩ ጠንካራና ተፎካካሪ ስፖርተኞችን የማፍራት አቅም እንዳለው ማሳያ ነው ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር እንዳሉት የዘንድሮው ስፖርታዊ ውድድር የሚያበረታታና የቀጣይ ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራት የሚያስችክ ነው ብለዋል።
በውድድሩ ስለተገኙ ድሎች እንዳብራሩት በአትሌቲክስ በወንድና በሴት 11 ወርቅ፣በ 8 ብር፣6 ነሐስ፣በጥቅሉ 25 ሜዳሊያዎችን በማምጣት ከክልሉ 1ኛ በመሆን ተጠናቋል፡፡
በፓራሊምፒክስ አትሌቲክስ በ 08 ወርቅ፣ 7 ብር ፣ 5 ነሐስ፣በአጠቃላይ 20 ሜዳሊያ በማምጣት በክልሉ በሴቶች አንደኛ እና በአጠቃላይ ውጤት ሁለተኛ ሆኖ ተጠናቋል፡፡
በቅርጫት ኳስ 1 የወርቅ ዋንጫ በማምጣት በአሸናፊነት ተደምድሟል።
በባህል ስፖርት ውድድር 3 ወርቅ፣4 ነሐስ፣ በድምሩ 7 ሜዳሊያ በማገኘት ከክልሉ 2ተኛ ሆነው ተጠናቋል፡፡
በወርልድ ቴኳንዶ 2 ወርቅ 3 ብር 6 ነሐስ በአጠቃላይ 11 ሜዳሊያ በመሰብሰብ የውድድሩ 2ተኛ ሆነው ተጠናቋል፡፡
በጠረጴዛ ቴኒስ 3 ወርቅ፣1ብር፤4 ነሐስ በአጠቃላይ 8 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በውድድሩ 2 ተኛ በመያዝ ተጠናቋል።
አቶ አደም ሽኩር አክለውም በዘንድሮው አመት ዞኑ በተሳተፈባቸው በ11 አይነት ውድድሮች በአጠቃላይ 32 የወርቅ ፣24 የብር እና 25 የነሐስ በአጠቃላይ 81 ልዩ ልዩ ሜዳሊያዎችንና 15 ዋንጫዎችን በማምጣት በክልሉ ካሉ ዞኖች 3ኛ በመሆን ማጠናቀቅ ገልጸው ለመላው ለጉራጌ ዞን ህዝብ ለተገኘው ድል እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

=== አካባቢህን ጠብቅ! ====
==== ወደ ግንባር ዝመት! ====
==== መከላከያን ደግፍ! ====
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *