የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አቶ መኩሪያ ተመስገን እንዳሉት መምሪያው አቅም ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዉያን እና ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን በዓልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ወቅት ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።
የአዲስ አመት በዓል ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካማና ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች፣ ወጣቶችና ስፖርት እና ሴቶችና ህፃናት መምሪያዎች በጋራ በመሆን የዱቄት፣ የዘይት የዶሮና የእንቁላል ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
እንደ ሀገር ብሎም እንደ ዞን የመደጋገፍ፣ ተካፍሎ የመብላት እሴት በማጠናከርና በማስቀጠል የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በየአካባቢው አረጋውያን፣ ጣሪ ደጋፊ የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን መኖራቸውን የተናገሩት አቶ መኩሪያ በዚህም ህብረተሰቡ በዓሉ በሚያከብርበት ወቅት ያለው ለሌለው የማህበረሰብ ክፍሎችን በማጋራት በጋር ማክበር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር መምሪያው በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከሌሎች ተቋማት በመቀናጀት አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማዕድ የማጋራት ስራ መሰራቱን አንስተዋል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋሙ ለአቅመ ደካሞች በተለያየ መልኩ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ ያለውን የመረዳዳትና የመተጋገዝ እሴት የበለጠ በማጎልበት በዞኑ ሁሉም ማህበረሰብ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በጋራ በመሆን በዓሉ ሊያከብሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉት በዓሉ ምክንያት በማድረግ የዞኑ መንግስት ባደረገላቸውን ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በዓሉ ለማክበር ምንም እንዳልነበራቸው ገልፀው የተደረገላቸው ድጋፍም በዓሉ በደስታ እንደሚያከብሩም አመላክተዋል።
አክለውም የዞኑ መንግስት ችግራቸውን በመረዳት ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።