የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በክልሉ ካሉ ምክር ቤቶች የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገቡ ለኮንታ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት ሉኡካን ቡድን ተሞክሮውን አካፈለ።

ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የህዝቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋልም።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ_ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አርሺያ አህመድ በልምድ ልውውጡ ወቅት እንደተናገሩት በተደረገው የልምድ ልውውጥ የመጣው አካል ብቻ ልምድ ቀስሞ የሚሄድ ብቻ ሳይሆን ከመጣውም አካል በርካታ ግብአት እንዳገኙ ገልጸዋል።
የዞኑ ምክር ቤት በ2013 ዓ.ም አበረታች ስራዎችን የተሰራ ሲሆን ጠንካራ ስራዎችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይም ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ስራ እንደሚሰሩ ወ/ሮ አርሺያ ተናግረዋል።
የዞኑ ምክር ቤት በህግ ከተሰጠውን ሀላፊነት አንፃር ህግ የማውጣትና የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን ማከናወን ሲሆን ከክትትልና ቁጥጥር ስራዎች አንፃር የተሻለ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ምክር ቤቱ በዞኑ የታቀዱ ስራዎችን ካለው ውስን በጀት ጋር ለማጣጣም የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡን የሚያነሷቸውን የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታው ላይ የተሻለ ስራ ለመስራት መታቀዱንም ተናግረዋል።
እንደ ወ/ሮ አርሺያ ገለፃ በቀጣይ ህብረተሰቡን የሚያነሷቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ፍትሃዊ፣ ተደራሽና ወቅታዊ በሆነ መልኩ ለመመለስ ምክር ቤቶች ጠንካራ የሆነ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎችን አጠናክረው መስራት አለባቸው ብለዋል።
አያይዘውም በሀገራችን የተቃጣውን የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሱ አካላት እንደጀመርነው በጋራ በመቆምና የህብረተሰቡን አንድነት በማጠናከር የጋራ ጠላታችን በማሸነፍ በአጭር ጌዜ ለሁላችንም ምቹ የሆነች ኢትዮጵያ ለመገንባት ጥረት ማድረግ አለብን ብለዋል።
የኮንታ ልዩ ወረዳ ም/ቤት የክትትል ቁጥጥር ሙያዊ ድጋፍ ዳይሬክተሬት አቶ ታዬ ተሰማና የኮንታ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እስራኤል ጮኬ በጋራ በሰጡት አስተያየት ከጉራጌ ዞን ምክር ቤት ጋር ባደረጉት የልምድድ ልውውጥ በርካታ ተሞክሮ እንደቀሰሙ ተናግረዋል።
ባገኙት ተሞክሮ በቀጣይ ወደ ልዩ ወረዳቸው በመውሰድ እንደሚሰሩ የተናገሩት አቶ እስራኤል ጮኬና አቶ ታዬ ተሰማ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አጠቃላይ የስራ
እንቅስቃሴ ለሌሎችም አካባቢዎች ተሞክሮ የሚሆን በመሆኑ ምክር ቤቱ ሊበረታታ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ለኮንታ ልዩ ወረዳ ምክር ቤት ስጦታ አበርክቷል ለሲል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *