ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለው በስራና በትግል መሆኑ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ገለፁ።
የጉራጌ ዞን ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ አርሺያ አህመድ ፎረሙን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት የምክርቤት ዋና ተግባር ህግ ማውጣትና የወጡ ህጎች እንዲተገበሩ በማድረግ የህዝቡ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ውክልናችንን በተግባር ማረጋገጥ ነው።
የምክር ቤት ዋና ተግባር አስፈፃሚውንና የዳኝነት አካሉን መከታተልና መቆጣጠር እንዲሁም በዋናነት በተቋሙ የህዝብ ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ እድገታችንን ሊያፋጥኑ የሚችሉ የታቀዱ እቅዶችን እንዲሳኩ ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ስራ መስራት ነው ሲሉ አፈጉባኤዋ ገልፀዋል ።
አሁን ካለንበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለመከላከያ ሰራዊታችን በጀመርነው ልክ ሁለንተናዊ ድጋፋችን ከሀሳብ እስከ መዝመት ከቁሳቁስ ድጋፍ እስከ ህይወት መሰዋእትነት በተዘጋጁ ልጆቿ ኢትዮጵያ እስክታሸንፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ በየደረጃው ያሉ ምክርቤቶች ሀላፊነታቸው ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የቀቤና ወረዳ ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ፈቱ ሙዘሚል እንደተናገሩት ወረዳቸው ይህ የዞኑ ምክርቤቶች ፎረም በማዘጋጀቱ ላቅ ያለ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል ።
የቀቤና ወረዳ ለቱሪዝሙና ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኑ ባለሀብቶች ገብተው ቢያለሙ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ አቶ ፈቱ አክለው ገልፀዋል።
በፎረሙ የተሳተፉ አካላት እንእደገለፁት የወክልነው ህዝብ ለማሳተፍና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በፎረሙ ያገኘነው ግብአት ወሳኝ ነው ብለዋል።
በፎረሙ የ2014 የጋራ የፎረም እቅድና በ2013 አፈፃፀም የነበሩ ማነቶዎችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ውይይትና ገምገማ በማድረግ የፀደቀ ሲሆን የቀጣይ የፎረም አዘጋጅ አበሽጌ ወረዳ መሆኑ ተገልፀዋል።
በመጨረሻም ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ የቀበሌና ከተማ ምክር ቤቶች እና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸው ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
አካባቢህን ጠብቅ፣
- ወደ ግንባር ዝመት፣
- መከላከያን ደግፍ።
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡ Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx