የጉራጌ ዞን ምክርቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 6ኛ አመት 20ኛ መደበኛ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አርሽያ አህመድ የምክርቤቱ ዋና አፈጉባኤ አድርጎ ሲሾም ለ2014 በጀት አመት ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።

በሀገሪቱ የተቃጣው ሀገር የማፍረስ ተግባር ለመመከት እየተደረገ ባለው ተግባር የዞኑ ህዝብ የጀመረው ሁሉም አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ምክርቤት አሳሰበ።የዞኑ ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ ክብርት ወይዘሮ አርሺያ አህመድ አሸባሪዎቹ የኦነግ ሸኔ እና የትህነግ ቡድኖች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የጀመሩት ሀገር የማፍረስ ተግባር ለመመከት መንግስት የጀመረው ህግ የማሰከበር ዘመቻ ለማጠናከር የዞኑ ህዝብ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።መላው የዞኑ ህዝብ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የገንዘብ፣ የደረቅ ምግብ እንዲሁም የሰንጋ በሬዎች ድጋፍ በማድረግ ያሳየው አገር ወዳድነቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።በተጠናቀቀው በጀት አመት ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከውስጥና ከውጭ የተለያዩ ችግሮ ቢገጥሟትም የዜጎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ እንደተቻለ ክብርት ወይዘሮ አርሺያ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ እያደገ ከመጣው የህዝቡ የመልማት ፍላጎት አኳያ ብዙ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።በአለም በከፍተኛ ፍጥነት በመዛመት የሰውን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባህሪውን እየቀያየረ የሚያጠቃ በመሆኑ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል እንደሚገባ አስረድተዋል።የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል የ2013 በጀት አመት የአፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በበጀት አመቱ በግብርና፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በመሰረተ ልማት ተደራሽነት እንዲሁም በትምህርትና የጤና ዘርፎች ላይ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ተብለዋል።እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ የዞኑ ህዝብ በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በተያዘው በጀት አመት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።የሰላምና ጸጥታ ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው በዞኑ ህገወጥ ተግባራት ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።አዳዲስና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ያሉት አቶ መሀመድ ዘርፉን ለማዘመን ትኩረት እንደሚሰጠው አስገንዝበዋል።አያይዘውም አስተዳዳሪው በወረዳዎች የሚስተዋለው የመንገድ ልማት ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራም ተናግረዋል።ምክርቤቱ ለ2014 በጀት አመት ከ4 ቢሊዮን 597 ሚሊዮን 426 ሺህ ብር ያጸደቀ ሲሆን በጀቱ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል።ጉባኤው የ2013 ዓ.ም የአስፈፃሚ ተቋማት፣የምክርቤቱና የፍርድቤቶች ተግባር አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን 2014 በጀት አመት ልዩ ልዩ እቅዶች ገምግሞ አፅድቀዋል።በመጨረሻም የምክርቤቱ ዋና አፈጉባኤ ጨምሮ የተለያዩ አስፈጻሚዎች እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በዚህም መሠረት1.አቶ መብራቴ ወ/ማሪያም ለጉራጌ ዞን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ 2.አቶ አወል ጅማቶ ለጉራጌ ዞን እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት መምሪያ 3.አቶ ሸምሱ አማን ለጉራጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ 4.ወ/ሮ አመተሩፍ ሁሴን ለጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት መምሪያ5.አቶ ፈለቀ ሀይሌ ለባህል ቱሪዝም ስፖርት ልማት መምሪያ በሀላፊነት ሾመዋል።ለወረዳና ለከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች1.አቶ ዘነበ ሰይፉ ለሶዶ ወረዳ 2. አቶ ዮሀንስ ውጅራን ለቸሀ ወረዳ3.አቶ ካሊድ በድሩን ለጉንችሬ ከተማ 4.አቶ አብረሀም መሀመድን ለእንድብር ከተማ5. አቶ ታረቀኝ ሻሚልን ለጌታ ወረዳ 6.አቶ አማረ ግዛቸውን ለመስቃን ወረዳ ፕሬዝዳንት አድርጎ በመሾም ተጠናቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *