የጉራጌ ዞን ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚሆን ድጋፍ ከ30 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሰንጋዎች፣ የበግና የፍየል ሙክቶችና ደረቅ ምግብ በሆለታ ከተማ ለኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ማስረከቡን ተገለጸ።

ጳጉሜ 04/2014 ዓ.ም

የጉራጌ ዞን ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚሆን ድጋፍ ከ30 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሰንጋዎች፣ የበግና የፍየል ሙክቶችና ደረቅ ምግብ በሆለታ ከተማ ለኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ማስረከቡን ተገለጸ።

አገር እያሸበረ ያለውን የህውኋት ቡድን እሰኪደመሰስ የዞኑ ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

በዛሬው ዕለት 3 መቶ 73 ሰንጋዎች 1 መቶ 59 የበግና የፍየል ሙክቶች፣ 96 ኩንታል ስኳር፣ 1መቶ 20 ኩንታል በሶ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የዛሬን ጨምሮ ከዞኑ ለ6ኛ ዙር ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረገኑ ተጠቁሟል።

በርክክብ ፕሮግራሙ ከፍተኛ የፌደራል ፣የክልል እንዲሁም የዞናችን ምክትል አስተዳደር አቶ አበራ ወንድሙ እና የሀብት አሰብሰብ የግብረሀይል አባላት ተገኝተዋል።

ዝርዝር መረጃ ይኖረናል ይጠብቁን።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *