የጉራጌ ዞንን ይጎብኙ! በጉራጌ ዞን ኢንቨስትም ያድርጉ!

ወደ ጉራጌ ዞን ከመጡ በቆይታዎ ተደስተው፣ መንፈሶ ታድሶ፣ በህዝቡ እንግዳ ተቀባይነት ተደምመው፣ በርካታ ተፈጥሮአዊ መስህቦችና ቅርሶች ጎብኝተው እና አዳዲስ የኢቭስትመንት አማራጮች ይዘው ይመለሳሉ።

የጉራጌ ዞን ምቹ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥና የአየር ፀባይ ያለዉ ሲሆን በርካታ ለቱሪዝም ልማት መሰረታዊ የሆኑ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ የቱሪስት መስህቦችና ቅርሶች ባለቤት ነው።

በዞኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ እ.ኤ.አ 1980 በዩኒስኮ የተመዘገበው የጥያ ትክል ድንጋይ መካነ ቅርስ ስፍራ እና በ20ዐ3 የተመዘገበው ግቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ መገኛ በመሆኑ በጎብኚዎች ተመራጭ ያደርገዋል ።

የጉራጌ ዞን ከአዲስ አበባ በ150 ኪሎ ሜትር በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ካሉት ከፍተኛ የቱሪስት መስህቦች ፣ ለጉብኝት ምቹ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ፣ የአየር ፀባይ፣ የተዘራበትን ሁሉ የሚያበቅል ለም መሬት፣ ሰላማዊና ስራ ወዳድ ማህበረሰብ ያለበት አካባቢ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ለኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ ያደርገዋል።

በዚህም በዞኑ ውስጥ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋያቸውን አፍሰው በሆቴል፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግና በመሳሰሉት የስራ መስኮች ተሰማርተው ውጤታማ የሆኑ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ህያው ምስክሮች ናቸው።

በዞኑ ከሚገኙ መስህቦች ዉስጥ በአለም ቅርስነት የተመዘገበዉ የጢያ ተክል ድንጋዮች መካነ ቅርስ ጨምሮ ፣ ግቤ ሸለቆ ብሄራዊ ፓርክ፣ ማራኪ ፏፏቴዎች፣ ፍል ዉሃዎች፣ በተፈጥሮ የተገኙ ታሪካዊ ይዘት ያላቸዉ ዋሻዎች፣ ጥብቅ የሀገር~በቀል የተፈጥሮ ደኖች፣ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ ገዳማትና መስጅዶች ወዘተ የሚጎበኙ ናቸዉ ።

በተጨማሪም ሀይቆች፣ የመዝናኛ ሎጅ፣ ጥንት አለም ሳይሰለጥን በጉራጌ ማህበረሰብ መሀንዲስ አባቶች የተቀመጠና የተጠበቀ ጆፎረ፣ የዋቤ ተፋሰስ መዝናኛና የዘቢዳር ሰንሰለታማ ተራሮች፣ ባህላዊ የቤት አሰራር ጥበብና ሌሎችም ይገኛሉ።

የማህበረሰቡ መለያ የሆኑት በባህላዊ አልባሳት፣ የጉራጌ ክትፎ፣ ቆጮና ቡና እንዲሁም ሌሎችም ምግብና መጠጦች ተጠቅመው ተዝናንተዉ የተንቢ፣ የብሳቢ፣ በላለዲ የምጣ፣ ሀበይ ወገሬቱ ተብለዉ ተቀብሎ በማስተናገድ በድንቅ የእንግዳ አቀባበል ባህል ተደምመው እርሶም ተደስተዉ ማህበረሰቡም ጠቅመዉ አዳዲስ የኢንቨስትመንት አማራጭ ይዘው ይመለሳሉ!

እናም ክቡራን ዳያስፓራችና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶቻችን ይምጡና ጉራጌ ዞንን ይጎብኙ!! በጉራጌ ዞን ኢንቭስትም ያድርጉ!

 የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች
              መምሪያ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *