የጉራጌ ብሔረሰብ ቱባ የስራና የቁጠባ ባህል በይበልጥ ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ከጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር በጉራጌ ብሔረሰብ የስራና የቁጠባ ባህል ረቂቅ የጥናት ሰነድ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት ተካሄደ።

የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ የባህል ታሪክ ቅርስ ጥናትና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጋጋዶ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን መካከል በክልሉ የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና ሌሎችም የባህልና ቱሪዝም ሀብቶችን ለማልማትና በሰነድ ተሰንዶ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ተቋማት ጋር ጥናቶችን እንዲጠና እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም በጉራጌ ብሔረሰብ የተጠናው የስራና የቁጠባ ባህል ረቂቅ የጥናት ሰነድ ለማስተቸት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የመረጃዎቹ ተአማኒነት ለማረጋገጥና የተጓደሉ ሃሳቦችን ለማካተትና ይበልጥ ፅሁፉ ለማዳበር ያለመ ወይይት እንደነበር ተናግረዋል።

እንደ አቶ መልካሙ ገለፃ የብሔረሰቡ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋዎችን ተሰንደው ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም የመንግስት አካላት፣ ማህበረሰቡና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አክለውም ለትችት የቀረበው ረቂቅ የጥናት ፅሁፍ ላይ የጎደሉ መረጃዎችን ተሟልተው የተሻለ ፅሁፍ ሆኖ ለህትመት እንዲቀርብ ሁሉም የብሄረሰቡ ሙህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸው እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ገ/መድህን በበኩላቸው ጉራጌ ለኢትዮጵያና ለአለም ህዝብ ካበረከታቸው እሴቶች መካከል ዕቁብ፣ እድርና እንዲሁም ከቁጠባ ጋር ግንኙነት ያላቸውና አሁን ላይ የአለም ህዝብ የሚጠቀሙዋቸውን ባንክና ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ መሰረት እንደሆኑ ተናግረዋል ።

በጉራጌ ብሔረሰብ የተጠናው ይህ የስራና የቁጠባ ረቂቅ ጥናታዊ ፅሁፍ ለትችት በማቅረብ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተጨማሪ ግብአት ለማሰባሰብ ያለመ ነው ብለዋል።

የብሄረሰቡ ታሪክ፣ ቋንቋና ባህልና ሌሎችም እሴቶችን ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ተመስገን በቀጣይም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም ከወልቂጤ ዩኒቨረሲቲ ጋር በመቀናጀት በትኩረት እንደሚሰሩም አስረድተዋል።

የመድረኩ ተሳተፊዎች እንደተናገሩት የቀረበው ረቂቅ ሰነድ የብሔረሰቡ ባህሎች፣ እሴቶችና ትውፊቶች በሰነድ ተሰንዶ ለትውልድ ለማስተላለፍ አይነተኛ ሚና ስላለው ጥናቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ተሳታፊዎች አክለውም የብሔረሰቡ ባህል፣ ቋንቋና እሴቶች በማሳደጉ ስራ ላይ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውና ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የባህል መሪዎችና የሀይማኖት አባቶች፣ ከብሔረሰቡ የተወጣጡ ሙህራን፣ የወጣትና የሴት አደረጃጀት ተወካዮች፣ ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

=== አካባቢህን ጠብቅ! ====
==== ወደ ግንባር ዝመት! ====
==== መከላከያን ደግፍ! ====

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *