የጉራጌ ብሔረሰብ ቱባ ባህላዊ እሴቶችን ተጠብቀው እንዲቆዪና እንዲለሙ ማድረግ ለሀገሪቷና ለዞኑ ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።


ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የሀገር በቀል እውቀቶችንና ባህል ልማት በጥናትና ምርምር በመለየት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በትኩረት እንደሚሰራ ገለፀ።

በጉራጌ ዞን አንትሮሽት ወይም የእናቶች የምስጋና ቀን በዓል “እናቶችን ማክበር ሀገርን ማክበር ነው” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች በወልቂጤ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ በበዓሉ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት አንትሮሽት የእናቶች የምስጋና በአል ከጥንት ጀምሮ በዞኑ በድምቀት የሚከበር በዓል መሆኑን ገልፀው በማህበረሰቡ ዘንድ በልዩ ትኩረት የሚከበርና በእናቶችም ይሁን በልጆች በጉጉት የሚጠበቅ በዓል እንደሆነም ገልፀዋል።

የጉራጌ ብሔረሰብ ቱባ ባህላዊ እሴቶችን በማህበረሰቡ ውስጥ ትውፊታቸውን ጠብቀው በማልማት ለሀገሪቷ ብሎም ለዞኑ ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲውሉ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

አክውም በዓሉ የጉራጌ ብሔር ለሴት ልጆችና ለእናቶች ያለውን ክብር ልዩና ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ በዚህም ቀን ለእናቶች ልዩ ክብር ይሰጣል ብለዋል።

በጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ የእናቶች ቀን ልዩ በመሆኑ አሁን ከደረስንበት ደረጃ ከፍ በማድረግ በደመቀና ሁሉን ባሳተፈ መልኩ በማልማት፣ በማክበር የመላ ኢትዮጵያውያንና የአለም በዓል እንዲሆን በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል እንደገለፁት አንትሮሽት እጅግ ውብ የሚያደርገው በተለይ ስልጣኔ ባልነበረበት ከረጅም ዘመናት በፊት ለሴቶች ነፃነትና መብት ታጋይ የነበረችው የጉራጌ ሴቶች ጀግና እናት የቃቄ ውርድወት ትኖርበት በነበረው በጉራጌ ዞን የሚከበር መሆኑ ነው ብለዋል።

ማርች -8 በአለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች ቀን እንደሚከበር ሁሉ የአንትሮሽት ወይም የእናቶች በዓል ቀን በሁሉም የጉራጌ አካባቢዎች በወጥነት ሊከበር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች አካል የሆነው ሀገር በቀል እውቀቶችና ባህል ልማት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በትኩረት እየሰራ ገልፀው አንትሮሽት በጥናትና ምርምር ተለይተው እንዲለሙ እየተደረጉ ካሉ የባህል እሴቶቻችን ውስጥ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ዶክተር ፍሪስ ገለፃ በዞኑ ምርቱ እየተመናመነ የሚገኘው እንሰት ከበዓሉ ጋር በማስተሳሰር የተሻለ እንሰት አምራች በሆኑ ወረዳዎችና በተመረጡ እናቶች ቤት እንዲከበርና ትውፊቱ እንዳይለቅ ለማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም የወልቂጤ ዩንቨርስቲ የበኩሉን እንደሚወጣ አመላክተዋል።

የጉራጌ ዞን ሴቶች ህፃናት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው አንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን በወርሃ ጥር የሚከበር በመሆኑ በዚህ በዓል እናቶች የሚደሰቱበት፣ ደረታቸው በቂቤ የሚለቀለቁበት፣ እናቶች እረፍት የሚያደርጉበት በዓል ነው ብለዋል።

አክለውም ይህ በዓል ዘመናዊነት ከመስፋፋቱ አንፃር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ገልፀው ችግሩንም ለመቅረፍ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ከቱባ ባህሉ አንፃር በዚህ ደረጃ በቂ ባለመሆኑ በሁሉም በዞኑ መዋቅሮችና በእናቶች ቤት እንዲከበር ሰፊ ስራ መሰራት አለበት ያሉት ወይዘሮ መሰረት ይህንንም በቲያትርና በዶክመንተሪ ፊልም መልኩ ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል። ሀገር በቀል የሆኑ ባህሎችን እንዲለሙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የድርሻቸውን እንደሚወጡም ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ወይዘሮ ዘይዳ ግዛውና ወይዘሮ እስከዳር ሲሳይ የበዓሉ ተሳታፊ ሲሆኑ በጋራ በሰጡት አስተያየት አንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን በዓል እናቶች በእንሰት መትከልና መፋቅ፣ ከበርካታ ውጣ ውረዶች በኃላ እናት በባለቤቷ መልካም ፈቃደኝነት ሰውነቷ ቅቤ ፈሶባት፣ ታርዶላት ዘመድ አዝማድና ጎርቤት ተጠርቶ የምትበላበት የምትጠጣበትና እረፍት የምታደርግበት ቀን መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም ቅድመ አያቶቻችን ያቆዩልንን ባህሎችን ሳይበረዝ ለቀጣይ ትውልድ ለማቆየት ወጣቶች፣ ምሁራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አስረድተዋል። በአሉንም ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶ በዞኑ በሁሉም አከባቢ መከበር አለበት ብለዋል።

በፕሮግራሙም የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከተፍተኛ አመራሮች፣ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ሙሁራን፣ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ሞዴል እማዎራዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመጨረሻም በወልቂጤ ዩንቨርስቲ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቀጣይ አመት የአንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን አዘጋጅ ቸሃ ወረዳ እንደንሆነም ተጠቁሟል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

ወቅታዊ ዜናዎች፣ዞናዊና አገራዊ መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሶት ገጻችን መውደድ፣ ለወዳጅዎ ማጋራት፣ አስተያየት መስጠት አይርሱ!!

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *