የጉራጌ ቡና የራሱ ብራንድ ወይም መለያ አግኝቶ ወደ ማእከላዊ ገበያ እንዲገባ እውቅና ተሰጥቶት በዘርፉ ለተሰማሩ አካላትም ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚሰራ የደቡብ ክልል የቡናና ቅመማቅመም ባለስልጣን ገለፀ።

የጉራጌ ቡና በስፋትና በጥራት በማምረት ማእከላዊ ገበያ ቀርቦ የአርሶአደሩ እና የዞኑ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲሻሻል በቅንጅት መሰራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለፀ።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዞኑ ቸሀና እነሞርና ኤነር ወረዳ እየለሙ የሚገኙ የአርሶ አደር የቡና ማሳዎች፣የመንግስትና የግል የቡና ችግኝ ማፊያ ጣቢያዎች የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

በመስክ ጉብኝቱ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለፁት በዞኑ ቡና አምራች አርሶ አደሮችን በመደገፍ፣ በማደራጀትና ዘመናዊ የግብይት ስርአት በማጠናከር ተጠቃሚነታቸው ይልበልጥ ለማሳደግ ይሰራል።

በቀጣይም ቡናን የማምረት ተግባር ወደ ሁሉም ወረዳዎች እንዲሰፋ በርካታ መከናወን ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ የገለፁት አስተዳዳሪው አመራሩ የጉራጌ ቡና ለተሻለ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውል እና ወደ ማእከላዊ ገበያ በስፋት እንዲገባ ትኩረት ሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል ።

አስተዳዳሪው አክለውም በቀጣይ በየደረጃው ያለው አመራር ለዘርፉ ተገቢ ትኩረት ሰጥቶ ሊመራው እንደሚገባም አሳስበዋል።

በደቡብ ክልል የቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ተፈራ ዘርፉ እንደገለፁት ቡናን በአግባቡ ለማልማት እና ምርታማ የሆነ ቡና አርሶ አደሩ እንዲያለማ በባለሙያ የሚደገፍ ዘመናዊ የችግኝ ጣቢያ መኖር አስፈላጊ ነው።

ይህ በጉራጌ ዞን በቸሃና እነሞር ኤነር ወረዳዎች ላይ መመልከት ችለናል ብለዋል።

እንደገለፁትታማነት ለማሳደግ በሌሎችም ወረዳዎች ላይ በባለሙያ በተገቢ በመደገፍ ውጤታማ ይሆናል የሚሉት አቶ ተፈራ ጥራትን ለማሻሻልና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደ ክልልም ሆነ እንደ ጉራጌ ዞን ወረዳዎች ጥረቱ ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አክለውም ሀላፊው የጉራጌ ቡና የራሱ ብራንድ ወይም መለያ አግኝቶ ወደ ገበያ እንዲገባ እውቅና ተሰጥቶት በዘርፉ ለተሰማሩ አካላትም ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቅንጅት እንደሚሰራም ጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንደገለፁት በዞናችን ካለው እምቅ የቡና አቅም ጋር ተያይዞ ሶስት ስፔሻላይዝድ ያደረጉ ወረዳዎች እንዳሉ ገልፀው በዞኑ ከ 50 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በቡና እየለማ ነው ተብለዋል።

ከዚህም ውስጥ በዘንድሮው የምርት ዘመን 30 ሺህ ሔክታር ያህሉ ማሳ ምርት እንደሚሰጥ ይታሰባል የሚሉት አቶ አበራ 115 ሺህ አርሶ አደሮች የቡና ምርት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ አበራ አክለው ዞናችን በቡና ልማቱና በግብይቱ እንዲታወቅ መስራት እና አግሮ ኢኮሎጂው የሚፈቅደውን የቡና ዝርያ በማምጣት ከገቢ አማራጮቻችን አንዱና ዋንኛው ቡና ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በጉብኝቱ የተገኙት ግብአቶች መነሻነት ቀጣይ መታረም በሚገባቸው ጉዳዮች፣የቡና ግብይት ዙርያ እንዲሁም የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን በመከላከል ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርገዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *