የጉራጌ ሕዝብ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው – ጠ/ ሚ ዓቢይ አህመድ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ከጉራጌ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው ብለዋል።

“ዛሬ ባደረግናቸው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ” ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በየደረጃው ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንሠራለንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *