የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር (ጉልባማ) 10ኛውን ዙር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በመስቃን ወረዳ እያካሄደ ይገኛል።

በጉራጌ ዞን ”ጉዞ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት” በሚል መሪ ቃል በየ አመቱ ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች ተተክለዋል።

ህብረተሰቡ የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ በመኮትኮትና ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ነጻ በማድረግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

“ጉዞ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ” ከችግኝ ተከላው ባለፈ የህብረተሰቡ የእርስ በርስ መስተጋብር እንዲጠናከርና በአካባቢው ልማት በንቃት እንዲሳተፍ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የጉልባማ 10ኛውን የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በመስቃን ወረዳ ዲራማ ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል።

በፕሮግራሙ ከፌደራል፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከደቡብ ክልል፣ ከጉራጌ ዞንና ወረዳዎች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶች፣ አትሌቶች፣ ባለሀብቶችና ሌሎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የዞኑ ተወላጆች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *