የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር (ጉልባማ) የዞኑን ህብረተሰብ የሚመጥን የልማት፣ የቋንቋና የባህል ስራዎች እንዲያከናውን ሁሉም የድርሻውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ጥሪ ቀረበ።

በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳድሮች ልማት ማህበሩን ለማጠናከር የተዘጋጁ የውይይት መድረኮች ማጠቃለያ ሪፖርት በወልቂጤ ከተማ ተገመገመ።

ጉልባማ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች እያከናወነ የሚገኝ ቢሆንም ከህብረተሰቡ ፍላጎት አኳያ ግን ብዙ መስራት ይጠበቅበታል።

የልማት ማህበሩ አቅም ለማጎልበት ከአመራሮች፣ ከመንግስት ሰራተኞች ፣ ከመምህራን፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ባለሀብቶችና
ከሌሎች ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል የውይይት መድረኮቹ ማጠቃለያ ሪፖርት በቀረበበት ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት አመታት ልማት ማህበሩን ቀርበን ባለመደገፋችን የሚጠበቅበትን ያክል ስራ መስራትና ዉጤት ማምጣት አልቻለም።

ጠንካራ የልማት፧ ማህበር መፍጠር የህዝቡ የልማት ተጠቃሚነትን ከማሳደግ በተጨማሪ አንድነቱና ባህላዊ እሴቶቹ እንዲጎለብቱ የሚያደርግ በመሆኑ የዞኑ አመራሮች ልማት ማህበሩን በበላይነት ሊደገፉት ይገባል ብለዋል።

እንደ አቶ መሀመድ ገለፃ ልማት ማህበሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከፍተኛ እንዲሆን በማድረግና ማህበሩ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲያመጣ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

ማህበሩ መንግስት ባልደረሰባቸው አካባቢዎች እያከናወናቸው የሚገኙ የልማት ስራዎች በማስተዋወቅና ህብረተሰቡ ስለማህበሩ መረጃ እንዲኖረው በስፋት መስራት ይገባል።

ልማት ማህበሩ ከልማት ስራዎች በተጨማሪ የህብረተሰቡን ትስስር የሚያጠናክር በመሆኑ መምህራን፣ ፐብሊክ ሰርቫንት፣ የንግዱ ማህበረሰብና አርሶ አደሮች በንቃት እንዲሳተፉ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ ከደረጃ “ሐ” ጀምሮ ከአመታዊ የስራ ግብር ጋር የአባልነት መዋጮ የሚከፍሉበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል ብለዋል።

የጉልባማ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ በበኩላቸው የልማት ማህበሩ አቅም ይበልጥ ለማጠናከር ከዞንና ወረዳ አመራሮች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑም ገልጸዋል።

የጉልባማ የገቢ ምንጭ ለማሳደግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ግንባታ ለማስጨረስ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ቅባቱ ማህበሩ በሚፈለገዉ ልክ ለዉጥ እንዲያመጣ የሁሉም ሰዉ ተሳትፎና ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

ማህበሩ የሚጠበቅበትን ስራ ለመስራት የሚያስችል አቅም እንዲኖረው ከዞኑ አመራሮችና ባለሞያዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት፣ በተቋሙ ሪፎርም ማድረግ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የጎሳና የአካባቢ አደረጃጀቶች በልማት ማህበሩ እንዲታቀፉ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ልማት ማህበሩ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት እንዲተዋወቁ የሚዲያ ስራዎች ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ህብረተሰቡ በማህበሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ እንዲጠናከር በቀበሌ ደረጃ ኮንፈረንስ እንዲካሄድ በማድረግ ህብረተሰቡ ማሳተፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ የግንዛቤ እጥረት፣ የአመለካከት ችግርና የመረጃ እጥረት እንዲቀረፉ መድረኮቹ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።

በመሆኑም ከሀምሌ ወር ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ መምህራንና አርሶ አደሮች እንዲሁም የክልል ተቋማት፣ የግልና የመንግስት ባንክ ሰራተኞች ጨምሮ የአባልነት መዋጮ መክፈል እንደሚጀምሩም ተሳታፊዎቹ ገለጹ።

እያንዳንዱ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ከአባላቱ የሚሰበሰበውን ገንዘብ ለልማት ማህበሩ ገቢ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መምከር እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *