የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር በውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆችን በአንድነት በማሰባሰብ ብሔረሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ የልማት ስራዎችን ለመስራት ነው፤ ክቡር ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው

ይህን ያሉት የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር አመታዊ ጉባኤው የብሔረሰቡ ተወላጆች በተገኙበት በአዱስ አበባ እያካሄደ በሚኝበት ወቅት ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በጉባኤው ላይ እንዳሉት የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር በውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ የጉራጌ ተወላጆችን በአንድነት በማሰባሰብ ብሔረሰቡ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ የልማት ስራዎችን ለመስራት ነው።

የጉራጌ ብሔረሰብ ማንነቱን ጠብቆና አንድነቱን አጠናክሮ በላቀ መሰረት ላይ ለመገንባት ልማት ማህበሩ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በዚህም በየክፍለ ህዝቡ ተበጣጥሶ ያሉ አደረጃጀቶች በመደመር እሳቤ ወደ አንድነት በማምጣት ጠንካራ የልማትና የባህል ማህበር ለመፍጠር መሆኑን አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ።

የጉራጌ ብሔረሰብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለውን ውህደትና በጋራ ማደግን መሰረት አድርጎ እንደሚንቀሳቀስ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አመለከቱ።

የልማትና የባህል ማህበሩ ብሔረሰቡ ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የልማት ስራዎችን ማከናወኑን የገለጹት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ ጉልባማ በሚያወጣው የልማት ፕሮግራም መሰረት የተጀመሩትን ልማቶች አጠናቆ አዳዲስ ለመጀመር መላው የጉራጌ ተወላጆች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ገብረ ስላሴ በበኩላቸው የጉራጌ ህዝብ በአንድ የማንነት አስተሳሰብና የመልማት ፍላጎት በሁለት የዞን መዋቅር ተደራጅቶ በላቀ መናበብና ቅንጅት ለልማት በተሰለፈበት ወቅት የሚካሄድ ጉባኤ በመሆኑ በአዲስ መንፈስ ለስራ እንደሚያነሳሳ ተናግረዋል።

ማህበሩ በሁለቱም ዞኖች የአባላት መዋጮና የልማት ድርጅቶችን በማስተባበር የአረንጓዴ ልማት፣ የባህልና የኢኮኖሚ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ሺሰማ ገልጸዋል።

በባህልና ልማት ማህበሩ አዲስ አበባና ቡታጅራ ከተሞች የጀመራቸውን የባህል ህንፃዎች ለማጠናቀቅ ዕቅድ ያዘጋጀ በመሆኑ ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ወዶጆች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *