የጉራጌ ህዝብ ስለ አንድነት ያስተማረ ፤ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን ፤በአንድት የሚገኘውን ፀጋ በልምድ ፣በሕይወቱ የተገነዘበ ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡


የጉራጌ ህዝብ ስለ አንድነት ያስተማረ ፤ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን ፤በአንድት የሚገኘውን ፀጋ በልምድ ፣በሕይወቱ የተገነዘበ ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በርካታ የዞኑ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ÷ጉራጌ “ጎጎት”በተባለ ቃልኪዳኑ ስለ አንድነት ያስተማረ ፤ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን፤ በአንድት የሚገኘውን ፀጋ በልምድና በሕይወቱ የተገነዘበ ነው ብለዋል፡፡

ሊከፋፍሉን ፣ሊለዩን ፣ሊያባሉን ለሚፈልጉ፤ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል በእየለቱ ገንዘባቸውን እውቀታቸውን እና ጊዜያቸውን ለሚያጠፉ ጉራጌ አንድነት ሃይል ነው ብሎ ስለሚያምን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ህዝብ ተምሮ ለጠላቶቹ በር መክፈት የለበትም ብለዋል፡፡

እንዲሁም አንድነቱን ተብቆ እቺን ድንቅ ሀገር ለልጆቻችን አብልፅጎ ማሻገር እንድንችል የበኩሉን ሚና ሊጫወት ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ጉራጌ ስለ ሰላም ያስተምራል ፤በሰላም ይኖራል ፤ሰላምን ያስተጋባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሰላም ሳናስብ ሳንናገር ሰላምን ልንጎናፀፋት አንችልም ነው ያሉት፡፡

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጉራጌ ተምሮ ሰላምን አብዝተን የምንፈልግ፣ አብሮ ለመኖር ፤የበለፀገች የማትለምንን ኢትዮጵያ ለማየት ሁላችንም በጋራ መቆም እንድንችል እና የሳታችሁ ወንድሞቻችን ልቦና እንዲሰጣችሁ እኔ እና የወልቂጤ ህዝብ በጋራ መልዕክት እናስተላልፋለንም ብለዋል፡፡

የእኛ የቋንቋ፣ የባህል፣የአቀማመጥ ልዩነት ኢትዮጵያን የሚበትን መሆን የለበትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አንድነት እና አብሮነት ለመማር የጉራጌን ባህል መገንዘብ ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

ልዩ ልዩ ቋንቋ ብንናገር የተለያየ እምነት ቢኖረን እና ፆታችን ቢለያይ ኢትዮጵያ አንድ የምታደርገን ስለሆነች ለሌላ ተገዝተን ኢትዮጵያን የምንከፋፍል ሳይሆን ለኢትዮጵያ አንድነት በጋራ የምንቆም እንሁን ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
fbc

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *